ጤና | በማ ድመጥ መማር | DW | 14.11.2008
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

በማ ድመጥ መማር

ጤና

አድማጮች ጤናማ ሕይወትን መምራት ከፈለጉ መጻህፍትን ማንበብ የግድ አይላቸውም። በማዳመጥ መማር የሚያቀርባቸዉን ዝግጅቶች መከታተል የመጀመርያ እርምጃ ሊሆን ይችላል።

default

ጤና

በጤና ለመኖር ቀላሉ መንገድ

አፍሪቃ ውስጥ ጤነኛ ሆኖ መኖር ከባድ ፈተና ነው። የትም ቦታ የተለያዩ የጤና ስጋቶች አሉ። አድማጮች ጤናማ ሕይወትን መምራት ከፈለጉ መጻህፍትን ማንበብ የግድ አይላቸውም። በማዳመጥ መማር የሚያቀርባቸዉን ዝግጅቶች መከታተል የመጀመርያ እርምጃ ሊሆን ይችላል።

አፍሪቃ ውስጥ ወባ ቁጥር አንድ ገዳይ በሽታ ነው። በወባ ትንኝ አማካኝነት የሚተላለፈው የወባ በሽታ በየ30 ሰከንዱ የአንድ አፍሪቃዊ ሕፃን ሕይወት ይቀጥፋል። ሌሎች የጤና ችግሮችም አሉ። ምግብ በሙቀት ቶሎ ሊበሰብስ ይችላል። ውሃን አፍልቶ አለመጠጣት ታይፎይድ ለተባለ በሽታ ሊያጋልጠን ይችላል። ከልክ ያለፈ ውፍረት የበለፀጉ አገሮች ችግር ብቻ ሳይሆን አፍሪቃ ውስጥም በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፋ ነው።

ታሞ ከመማቀቅ አስቀድሞ መጠንቀቅ

አብዛኛዎቹን በሽታዎች አስቀድመን መከላከል እንችላለን። በርከት ያለው ሕዝብ ግን እውቀቱ የለውም። አንዳንድ ጊዜ ምግብን በአግባቡ መያዝና የግል ንፅህናን መጠበቅ በቂ ሊሆን ይችላል። በዝግጅቱ የሚቀርበው የሬድዮ ጭውውት አምስት ልጆች፤ በቤትና ከቤት ውጪ ሊያጋጥሙ የሚችሉ የጤና ስጋቶችን በመለየት ሊያስወግዷቸው የሚችሉባቸውን ቀላል መንገዶች በማንሳት ሲወያዩባቸው ያስደምጣል።

በማዳመጥ መማር የተሰኘው ዝግጅት በስድስት ቋንቋዎች ይቀርባል። ቋንቋዎቹም አማርኛ፣ ኪስዋሂሊ፣ ሃውሳ፣ ፈረንሳይኛ፣ እንግሊዝኛና ፖርቱጋልኛ ናቸው። ተጨማሪ መረጃ ወይም ዝግጅቶቹን ለማዳመጥ ከፈለጉ እባክዎንwww.dw-world.de/learning-by-ear የተሰኘውን ድረ ገጻችንን ይጎብኙ።በማድመጥ መማር የተሰኘው ፕሮጀክት በጀርመን ፌደራላዊ የውጪ ጉዳይ ሚ ኒስቴር ይታገዛል።