ጤናና አካባቢያችን በ2002ዓ,ም | ጤና እና አካባቢ | DW | 07.09.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ጤና እና አካባቢ

ጤናና አካባቢያችን በ2002ዓ,ም

በ2002ዓ,ም የተለያዩ ተስፋ ሰጪ ተግባራት በጤና አገልግሎትና በአካባቢ ተፈጥሮ ጥበቃ ረገድ መከናወናቸዉን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸዉ ወገኖች ይገልጻሉ።

default

በአሮጌዉ ዓመት የተጀመሩ አበረታች ተግባራት በመጪዉ ዓመት ይበልጥ ተስፋፍተዉ ዉጤት ለማየት ግን ጅምሩን አጠናክሮ ማስፋፋት ይጠይቃል። በገጠሪቱ ኢትዮጵያ የጤና አገልግሎትን ለማስፋፋት የተቀየሰዉ ስልት፤ የወባ በሽታን ለመቆጣጠር እንዳስቻለ ሁሉ፤ የእናቶችና ህፃናትን ሞት ይበልጥ በመቀነስ፤ የHIV AIDS ንም ስርጭት በመግታት፤ የተመድ ካለመዉ የልማት ግብ ለመድረስ መጣር ግድ ይሆናል። የተራቆቱ አካባቢዎችን ከሰዉና እንስሳት ንክኪ በማግለል ለማልማት የተጀመረዉ ጥረት፤ በጎነቱ ባያነጋግርም፤ የነበሩ የአገሪቱን ዉሱን የደን ሃብቶችምi በየደረጃዉ አላግባብ ከሚወድሙበት አካሄድ ማዳን ያስፈልጋል።

ሸዋዬ ለገሠ

ተክሌ የኋላ