ጤናማ አፈር ለጤናማ ህይወት | ጤና እና አካባቢ | DW | 17.11.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ጤና እና አካባቢ

ጤናማ አፈር ለጤናማ ህይወት

አፈር በየቦታዉ እንደልብ የሚገኝ የተፈጥሮ ሀብት በመሆኑ ብቻ ጥንቃቄና ክብካቤ እንደሚያስፈልገዉ ብዙዎች አይገነዘቡም። የዓለም የምግብ እና እርሻ ድርጅት FAO ዋና ዳይሬክተር ሆሴ ግራዚአኖ ደ ሲልቫ በዓለም ካለዉ ብዝሃ ሕይወት አፈር አንድ አራተኛዉን እጅ እንደሚይዝ መጠቆማቸዉን የድርጅቱ መረጃዎች ያመለክታሉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 10:37
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
10:37 ደቂቃ

ጤናማ አፈር ለጤናማ ህይወት

አፈር በብዛት ይገኛል ቢባልም ግን በተፈጥሮ አደጋዎችም ሆነ በሰዉ ሠራሽ ችግሮች የአፈር ለምነት እና ጤናማነት እያሽቆለቆለ መሄዱን የዘርፉ ባለሙያዎች ያስገነዝባሉ።

ይህ ደግሞ በአፈር አማክኝነት በቅሎ ለምግብነት የሚዉለዉ የሰብል ምርት እንዲቀነስ እና የምግብ ዋስትና ጥያቄ ላይ እንዲወድቅ ማድረጉ ይገለጻል። FAO የአፈር ለምነትና ጤናማነት ዘላቂነት እንዲኖረዉ መደረግ ስለሚገባቸዉ ተግባራት ሲዘረዝር፤ አብዛኛዉ ገበሬ የሚጠቀምበትን ባህላዊ የአፈር ክብካቤ ነዉ የሚያስቀድመዉ። ይህም ሰብልን መቀያየር የሚለዉ ነዉ። እንደFAO ይህ ስልት አፈር ያለዉን ጠቃሚ ንጥረነገር እያደሰና ዳግም እያመነጨ በለምነቱ እንዲቀጥል ይረዳዋል። «አፈር ድምፅ የለዉም።» ይላሉ ሆሴ ግራዚአኖ ደ ሲልቫ የዓለም የምግብ እና እርሻ ድርጅት FAO ዋና ዳይሬክተር። በምግብ ማምረት ሂደት ድምጽ አልባ የሆነዉ የሰዉ ልጆች ተጓዳኝ ስለሆነዉ አፈር እጅግ ጥቂት ሰዎች ናቸዉ የሚናገሩለት። አርቲስት ስለሺ ደምሴ ማለትም ጋሽ አበራ ሞላ፤ በኪነጥበብ ሥራዎች የአፈርን ጠቀሜታ በማስገንዘብ ለአፈር ጥንቃቄ እንዲደረግ የሚያሳስብ ዝግጅት ትናንት ማምሻዉን በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ከባልደረቦቹ ጋር በመሆን አቅርቧል።

ጤናማ አፈር ለጤናማ ሕይወት በሚል መርሕ ነዉ ይህ ጎርጎሪዮሳዊዉ 2015ዓ,ም በመላዉ ዓለም ለአፈር ትኩረት እንዲሰጥ የተመድ የወሰነዉ። ስለጤናማ አፈር ስንናገር ምን ማለታችን ይሆን? የአፈር ምርታማነት እንዲሻሻልም ሆነ ለምነቱ እንዳይጠፋ የአፈር ጤናማነት መጠበቅ እንደሚኖርበት በባለሙያዎች ተደጋግሞ ይገለፃል። የአፈር ጤናማነት እንዴት ነዉ የሚጠበቀዉ? በኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ተቋም የአፈርና ዉኃ ምርምር ዳይሬክቶሬት ምክትል ዳይሬክተር አቶ ገብረየስ ጉርሙ አብራርተዋል። ከድምጽ ዘገባዉ ያድምጡ!

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic