ጤናማ አመጋገብና የስኳር ሕመም | ጤና እና አካባቢ | DW | 11.11.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ጤና እና አካባቢ

ጤናማ አመጋገብና የስኳር ሕመም

በቅርቡ ይፋ የሆነ ሠነድ እንዳመለከተዉ በአሁኑ ወቅት በዓለማችን 382 የስኳር ሕሙማን አሉ። በዚያ ላይም 316 ሚሊዮን ሕዝብ 2ኛዉ ደረጃ (ታይፕ 2 ) ለሚባለዉ የስኳር ሕመም የመጋለጥ እድሉ ሰፊ እንደሆነ መረጃዉ ይጠቁሟል።

BdT Diabetes - Insulin

ወደፊት ማለትም ከ15 እና 16 ዓመታት በኋላ ደግሞ የስኳር ሕሙማን ቁጥር ወደ592 ሚሊዮን ከፍ እንደሚል ግምቱ አለ። ይህም በዓለም ደረጃ ከአስር ሰዎች አንዱ ማለት ነዉ። ቁጥሩ ከፍ የማለቱ ምክንያትም በአብዛኛዉ የዓለም ክፍል በሽታዉ ተደብቆ በመቆየቱ መሆኑን ዓለም ዓቀፍ የስኳር ሕመም ፌዴሬሽን አስፍሮታል። ፌዴሬሽኑ እንደሚለዉን እንደዉም ከስኳር ሕሙማን ግማሽ ያህሉ የሕመማቸዉ ምንነት ገና ይፋ አልሆነም። መረጃዎቹ ይፋ ባለመሆናቸዉም በተለይም በ2ኛ ደረጃ የሚገኘዉን የስኳር ሕመም ባለበት ደረጃ ላይ ለመቆጣጠር አፋጣኝ እርምጃ የመዉሰድ አስፈላጊነትን እንደሚማመላክት ነዉ የተገለጸዉ። መረጃዎች እንደሚመለክቱትም ጤናማ የአኗኗር ሁኔታ እና ጤናማ አካባቢ ሁለተኛዉ ዓይነት መሆኑ የሚገለጸዉ ማለትም ታይፕ 2 የሚባለዉን የስኳር ሕመም ከመከላከሉ በተጨማሪ በስኳር ሕመም ምክንያት የሚከተሉ ዉስብስብ የጤና ችግሮችን ለማስወገድ ይረዳል። በዚህ በሶስት ዓመቱ የዘመቻ እንቅስቃሴም እያንዳብዴ ሰዉ በሚያደርገዉ ጤናማ የአመጋገብና የአኗኗር ምርጫ የስኳር ሕመም ከሚያስከትላቸዉ የተለያዩ ችግሮች ራሱን እንደሚከላከል፤ በበሽታዉ ያልተያዘ ከሆነም ለዚያ እንዳይጋለጥ ወሳኝ መረጃዎች ለማዳረስ ጥረት ይደረጋል።

Diabetes Flash-Galerie

31ዓመታትን ያስቆጠረዉ የኢትዮጵያ የስኳር ሕመም ማኅበር የስኳር ሕሙማን በሽታዉን ስለሚከላከሉባቸዉ መንገዶች የሚማሩበት፤ እንዲሁም ለበሽታዉ የተጋለጡ ሁሉ መረጃዎችን እንዲያገኙበት ታቅዶ የተቋቋመ ነዉ። አባላት የሆኑ የስኳር ሕመምተኞቹ ቁጥር እየጨመረ መሄዱን ተከትሎም በዋና ከተማ ብቻ ሳይሆን በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞችበጎ ፈቃደኞች የሚመሯቸዉ 42 ቅርንጫፎች አሉት። በማሕበሩ የታቀፉትም አዋቂዎች ብቻ ሳይሆኑ ልጆችም የስኳር በሽታ የእድሜ ልክ ከሚባሉት አንዱ በመሆኑም ማኅበሩ ስለበሽታዉ አስፈላጊ መረጃዎችን በወር አንዴ በሚያካሂደዉ የትምህርት መድረክ ተጠቅሞ ገለጻዎችን ያደርጋል።

ወ/ሮ ምሥራቅ ታረቀኝ የኢትዮጵያ ስኳር መመም ማኅበር የሥራ መሪ/ፕሮግራም ማኔጀር/ ማኅበሩ የአባላቱን ቁጥር የሚያዉቀዉን ያህል በመላ ሀገሪቱ ምን ያህል የስኳር ሕሙማን እንዳሉ ለማወቅ ጥናቶች አለመኖራቸዉን ያመለክታሉ። ከዓለም ዓቀፍ የስክር ሕመም ፌዴሬሽን በተገኘዉ መረጃ መሠረት ግን 2 ሚሊዮን ይደርሳሉ። የኢትዮጵያዉ ማኅበር ደግሞ 20ሺ የሆኑ አባላት አሉት። የስኳር ሕሙማንን ቁጥር እንደኢትዮጵያ ባሉ ሃገራት በትክክል የማይታወቅበት ምክንያትም እንደወ/ሮ ምሥራት ተላላፊ ላልሆኑ በሽታዎች የሚሰጠዉን የትኩረት ሁኔታ ያመላክታል።

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic