ጣምራ የሥነ ተዋልዶ ጤናና ልማት ድርጅት | ባህል | DW | 23.08.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

ጣምራ የሥነ ተዋልዶ ጤናና ልማት ድርጅት

«ጣምራ የስነ ተዋልዶ ጤናና ልማት ድርጅት» ሻሸመኔ ውስጥ በወጣቶች የተቋቋመ እና ለወጣቶች የሚሠራ ድርጅት ነው።

Argobba - Kinder und Jugendliche in Tollaha Dorf 2012 Autor/Copyright: Azeb Tadesse Hahn, DW, 2012 Die Argobba sind eine ethnische Gruppe in Äthiopien. Sie sind Muslime und leben am östlichen Rand des äthiopischen Hochlandes sowie in der Umgebung der Stadt Harar. Ihre ursprüngliche Sprache, das Argobba, ist diejenige äthio-semitische Sprache, welche mit dem Amharischen am nächsten verwandt ist. Die Argobba glauben, dass sie von arabischen Einwanderern aus dem Stamm des Propheten Mohammed abstammen, die den Islam nach Äthiopien brachten.

Argobba – Tollaha Dorf Äthiopien

ከመሥራቾቹ አንዱ ብሩክ ይርጋለም ይባላል። የሚኖረው ተወልዶ ባደገበት ሻሸመኔ ከተማ ነው። በአሁኑ ሰዓት «ጣምራ የስነ ተዋልዶ ጤናና ልማት ድርጅት» ውስጥ የፕሮግራም አስተባባሪ ሆኖ ያገለግላል።

በሻሸመኔ ከተማ እያዝናኑ ማስተማር በሚል ፕሮግራማችን እንታወቃለን የሚለው ብሩክ፤ በስነ ጹሑፍ፣ ቲያትር ሙዚቃ እና ውዝዋዜ ዘርፍ ስር የሚካፈሉት ወጣቶች ትልቅ ቦታ ላይ ሲደርሱ መመልከታቸውን አይተናል ይላል። በ «ጣምራ የስነ ተዋልዶ ጤናና ልማት ድርጅት» ስር ያሉት ወጣቶች አብዛኞቹ በጎ ፍቃደኞች ናቸው።

«ጣምራ የስነ ተዋልዶ ጤናና ልማት ድርጅት» ለዚህ ስኬት ከማሕበረሰቡ ፣ ከመንግሥትም ይሁን ከተለያዩ መንግሥታዊ ያልሆኑ የውጭ በጎ አድራጎት ድርጅቶች ድጋፍ እና እውቅና ማግኘቱን ብሩክ ሳይገልፅ አላለፈም። በሻሸመኔ ከተማ የመጀመሪያውን የወጣት ማዕከል የመሠረቱት ወጣቶች በከተማቸው ሌሎች የወጣት ማዕከላት እንዲገነቡም አርአያ ለመሆን ችለዋል።

ብሩክ ስለ ድርጅቱ አጀማመር እና እንቅስቃሴ የገለፀልንን ከድምፅ ዘገባው ያገኙታል።

ልደት አበበ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic