ጠ/ሚንስትር መለስ ለህዝብ እንደራሴዎች የሰጡት መልስ
ሐሙስ፣ ጥቅምት 9 2004ማስታወቂያ
ለጠ/ሚንስትሩ ከቀረቡት በርካታ ጥያቄዎች መካከል፤ መግቻ ያጣው የዋጋ ግሽበትና የኑሮ ውድነት፤ የመልካም አስተዳደር እጦትና ሙስና፤ መንግሥት በቅርቡ፤ በተቃዋሚዎች ላይ በሽብርተኝነት እየፈረጀ የጀመረው እሥር፤ የመንግሥት የተለጠጠ የዕድገት ሽግግር (ትራንስፎርሜሽን) እቅድና ችግሮቹ፣ በዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ኀላፊዎች፤ ይኸው እቅድ፤ በችግር የተተበተበና እውን መሆን አይችልም ተብሎ የቀረበበት ትችት፤ በመንግሥት የግብር አሰባሰብ ህዝቡ እያሰማ ያለው ምሬትና እሮሮ፣ እንደ ከተማው መሬት ሁሉ በገጠርም ገንዘብን ሥራ ላይ ማዋል (ኢንቤስትመንት) በሚል ስም የተስፋፋው የመሬት ወረራ የተሰኙት ዋናዋናዎቹ ነበሩ----።
ታደሰ አንግዳው
ተክሌ የኋላ
ሂሩት መለሰ