ጠቅላይ ምኒስትር አብይ አሕመድ ሥልጣን ተረከቡ | ኢትዮጵያ | DW | 02.04.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ጠቅላይ ምኒስትር አብይ አሕመድ ሥልጣን ተረከቡ

የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢሕአዴግ ሊቀ-መንበር ዶክተር አብይ አሕመድን ጠቅላይ ምኒስትር አድርጎ ሾመ። የጠቅላይ ምኒስትሩን ሹመት ለምክር ቤቱ ያቀረቡት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ናቸው። የቀድሞው ጠቅላይ ምኒስትር በይፋ ሥልጣናቸውን ለአዲሱ ጠቅላይ ምኒስትር አስረክበዋል።

የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢሕአዴግ ሊቀ-መንበር ዶክተር አብይ አሕመድን ጠቅላይ ምኒስትር አድርጎ ሾመ። የጠቅላይ ምኒስትሩን ሹመት ለምክር ቤቱ ያቀረቡት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ናቸው። የቀድሞው ጠቅላይ ምኒስትር በይፋ ሥልጣናቸውን ለአዲሱ ጠቅላይ ምኒስትር አስረክበዋል።

ጠቅላይ ምኒስትር አብይ በምክር ቤቱ ባሰሙት ንግግር "በርካታ ጉድለቶች እንዳሉ እናምናለን" ሲሉ ተናግረዋል። "ወቅቱ ከስህተታችን ተምረን አገራችንን የምንክስበት ነው" ያሉት ጠቅላይ ምኒስትሩ የሕግ የበላይነትን ለማስፈን ቃል-ገብተዋል።

ጠቅላይ ምኒስትሩ ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማሻሻል እሰራለሁ ብለዋል። የኤርትራ መንግሥትም በሁለቱ አገሮች መካከል ያለውን ልዩነት ለመፍታት እንዲሰራ ጥሪ አቅርበዋል። 

እሸቴ በቀለ