ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ከቦንጋ ነዋሪዎች ጋር ተወያዩ | ኢትዮጵያ | DW | 16.09.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ከቦንጋ ነዋሪዎች ጋር ተወያዩ

የሸካ ሕዝብ የክልል እንሁን ጥያቄዉን በሰላማዊ መንገድ ማቅረቡ እንደሚያደንቁ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ ገለፁ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን የተናገሩት ትናንት በካፋ ሸካ ከሃገር ሽማግሌዎች እና ነዋሪዎች ጋር ባደረጉት ዉይይት ላይ ነዉ ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 05:03

የመሰረተ ልማት ጥያቄዎች እንደሚፈቱ ቃል ገብተዋል

የሸካ ሕዝብ የክልል እንሁን ጥያቄዉን በሰላማዊ መንገድ ማቅረቡ እንደሚያደንቁ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ ገለፁ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን የተናገሩት ትናንት በካፋ ሸካ  ከሃገር ሽማግሌዎች እና ነዋሪዎች ጋር ባደረጉት ዉይይት ላይ ነዉ ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለቀረቡት የመሰረተ ልማት ጥያቄዎች ከመንግሥታቸዉ ጋር ተመካክረዉ እንደሚፈቱም ቃል ገብተዋል። በእለቱ ክልል ኃላፊዎች በተጨማሪ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸዉ፤  ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እና የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ለማ መገርሳ ተገኝተዉ ነበር። ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ወደ ቦንጋ የተጓዘዉ ወኪላችን ዮኃንስ ገብረግዚአብሔር ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል። 

ዮኃንስ ገብረግዚአብሔር

አዜብ ታደሰ

ኂሩት መለሰ    

Audios and videos on the topic