ጠቅላላ እውቀት | ራድዮ | DW | 22.10.2008
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ራድዮ

ጠቅላላ እውቀት

የጽሑፍ መልእክት ኤ ስ ኤም ኤስ ከአንድ ተንቀሳቃሽ ስልክ ወደሌላ መተላለፍ እንደሚችል የሚ ያውቁ ጥቂት ሰዎች ብቻ ናቸው። የመኪና ጎማ ለምን ጥቁር እንደሚ ሆን የሚረዱት ሰዎች ቁጥር ደግሞ ከዛ ያነስ ነዉ

default

የቀን-ተቀን ምትሃቶች

የቀን-ተቀን ምትሃቶች

የምንኖርባት ዓለም ልናስበው ከምንችለው በላይ ምስጢራዊ በሆኑ ነገሮች የተሞላች ነች። የጽሑፍ መልእክት ኤ ስ ኤም ኤስ ከአንድ ተንቀሳቃሽ ስልክ ወደሌላ መተላለፍ እንደሚችል የሚ ያውቁ ጥቂት ሰዎች ብቻ ናቸው። የመኪና ጎማ ለምን ጥቁር እንደሚ ሆን የሚረዱት ሰዎች ቁጥር ደግሞ ከዛ ያነስ ነዉ

በማዳመጥ መማር የተሰኘው ዝግጅታችን አድማጮችን ወደቀን-ተቀን ሕይወታቸው ይወስዳቸዋል። ይህ ዝግጅት ትምህርት ቤት ውስጥ ብዙም ውይይት የማይደረግባቸው ምስጢራዊ ጉዳዮችን ይዳስሳል። ለምሳሌ ዘጋቢዎቻችን ለዕቃ መያዣ የምንጠቀምባቸው ፌስታሎች እንዴት እንደሚሰሩና አካባቢያችንን እንዴት ሊበክሉ እንደሚችሉ ባለሙያ አወያይተው ያስረዱናል።

መሰረታዊ ጉዳዮችና ክስተቶች

ዝግጅቶቻችን ሰዎች ፍቅር ሲይዛቸው እንዲሁም እንስሳት በአካባቢያቸው ያላቸውን የሕይወት ሁኔታ ያሳያል። የተለያዩ ክስተቶችም ለምሳሌ ድንች በሚበስልበት ጊዜ ለምን እንደሚለሰልስ በአንፃሩ እንቁላል ለምን እንደሚጠነክር እንመለከታለን። በእውቀት ክምር ተከበናል። በማዳመጥ መማር የተሰኘውን ዝግጅት በመከታተል አድማጮች የተለያዩ ነገሮችን ለመረዳት እድል ያገኛሉ።

በማዳመጥ መማር የተሰኘው ዝግጅት በስድስት ቋንቋዎች ማለትም በአማርኛ፣ ኪስዋሂሊ፣ ሃውሳ፣ ፈረንሳይኛ፣ እንግሊዝኛና ፖርቱጋልኛ ይቀርባል። ተጨማሪ መረጃ ወይም ዝግጅቶቹን ደግመው ለማዳመጥ ከፈለጉ እባክዎንየተሰኘውን ድረ ገጻችንን ይጎብኙ።በማዳመጥ መማር የተሰኘው ፕሮጀክት በጀርመን ፌደራላዊ የውጪ ጉዳይ ሚ ኒስቴር ይታገዛል።

Audios and videos on the topic