ጎጂ ልማድ እንደ ባህል | ባህል | DW | 07.02.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

ጎጂ ልማድ እንደ ባህል

ጎርጎሪዮሳዊው ጥር 6 የሴት ልጅ ግርዛት የሚወገዝበት የአለም አቀፍ ቀን ነው። የሴት ልጅ ግርዛት ጎጂ ልማድ እንደሆነ እየታወቀ ኢትዮጵያ ውስጥም እንደ ባህል አሁን ድረስ ይፈፀማል።

በዓለም ላይ በዛሬዋ ዕለት  ምን አልባት በምላጭ አልያም በቢላዋ፣ በጠርሙስ ስባሪ ወይንም በቆርቆሮ ቁራጭ የተገረዘች ህፃን አትጠፋም። ከትውልድ ትውልድ ተላልፎ በመፈፀሙ አንዳንዶችም ባህላችን ብለው የሚጠሩት በሴቶች ላይ የሚፈፀም ግርዛት እንደ ቦታው ይለያያል።

Demonstration einer Kampagne gegen Genitalverstümmelung (FGM) in Guinea-Bissau. Auf dem Plakt steht: Es lebe die Tradition, weg mit der Beschneidung. Copyright: Weltfriedensdienst e.V. Aufnahmedatum: September 2011 ***ACHTUNG: Bild darf nur im Rahmen der Berichterstattung der DW über FGM verwendet werden.***

የሴት ልጅ ግርዛትን በጊኒ ቢሳው ሲቃወሙ

«የተፈፀመው አንድ ፀጉር ቤት ውስጥ ነው። አንድ ቀን ወላጆች በሙሉ በሰፈሩ በእኔ እድሜ ክልል የነበሩ ልጃ ገረዶችን ሰብስበው ሰውየው ጋ ወሰዱን። እኛ ለምን እንደሆነ አላወቅንም ነበር። ደስ ብሎን ነበር። ምክንያቱም ለበዓሉ እጃችንን ሂና ተቀብተን ነበር በዛ ላይ የዶሮ ሾርባ ተሰጠን። በጣም ደስ ብሎን ነበር። »ትላለች ግብፃዊቷ ኡነ መሀመድ። ኡነ የ12 ሁለት አመት ልጅ ሳለች እንደሌሎች አብረዋት የነበሩት የሰፈሯ ልጆች ወንጀል ተፈፅሞባታል። ይህ ህመም ብቻ ሳይሆን  በአዕምሮዋም ትቶ ያለፈው ነገር አለ።

ARCHIV - Waris Dirie, somalisches Topmodel und Unicef-Botschafterin, auf einer Pressekonferenz in Hamburg (Archivfoto vom 08.06.2004). Top-Model und Menschenrechtlerin Waris Dirie erhält für ihren Einsatz gegen Genitalverstümmelung die deutsch-niederländische Martin-Buber-Plakette. Mit ihrer in Wien gegründeten Stiftung und als UN-Sonderbotschafterin kämpft sie für die Abschaffung der Beschneidung von Mädchen und für die Anerkennung drohender Genitalverstümmelung als Asylgrund. Die Verleihung findet am 30. November im niederländischen Kerkrade bei Aachen statt. Foto: Kay Nietfeld dpa/lnw +++(c) dpa - Bildfunk+++

ሶማላዊቷ ዋሪስ ዲሬ የሴት ልጅ ግርዛት እንዲቆም ትልቅ ሚና ተጫውታለች

« ለሶስት ቀናት እደማ ነበር። ታድያ ደጋግሜ ራሴን እጠይቀው የነበረው ነገር ቢኖር ምን ባጠፋ ነው ወላጆቼ ይህንን ያደረጉብኝ የሚል ነበር። አንዲት ልጅ እንደውም በዚህ የተነሳ ህይወቷ አልፏል።»ኡነ ብቻዋን አይደለችም። በአለም ዙሪያ ከ130-150 ሚሊዮን የሚሆኑ የሴት ልጅ ግርዛት ሰለባ መሆናቸው ይነገራል። አብዛኞቹ አፍሪቃ ውስጥ ናቸው። በአንዳንድ ሀገራት በህግ የሚያስቀጣ ሆኖም በ29 የአፍሪቃ ሀገራት የሴት ልጅ ግርዛት ይፈፀማል። ከነዚህ ሀገራት አንዷ ኢትዮጵያ ናት።

ጀርመን ውስጥም የሴት ልጅ ግርዛት ይፈፀማል። ፈፃሚ እና አስፈፃሚዎቹ ግን የውጭ ሀገር ዜጎች ናቸው። ማንም ይሁን ማን ድርጊቱ በጀርመን ህግም ያስቀጣል። ወላጆችም የማሳደግ መብታቸውን ያጣሉ። የቅጣቱ አይነት ይለያይ እንጂ  ይህም በኢትዮጵያ መቅጫ ህግ ሰፍሯል። ለመሆኑ ህጉ ምን ያህል በተግባር ላይ ይውላል? በኢትዮጵያ በወቅቱ የሴት ልጅ ግርዛትን በተመለከተ ያለውንስ ሁኔታ ምን ይመስላል። ለዚህ እና ለሌሎች ጥቃቄዎች መልስ ለማግኘት የኢትዮጵያ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች አስወጋጅ ማህበር ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አሊ ሀሰንን አነጋግረናል።

ልደት አበበ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic