ግጭት በኦሮሚያና በኢትዮጵያ ሶማሌ አዋሳኝ ድንበር    | ኢትዮጵያ | DW | 07.05.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ግጭት በኦሮሚያና በኢትዮጵያ ሶማሌ አዋሳኝ ድንበር   

በትላንትናዉ እለት በኢትዮጵያ ሞያሌ ዉስጥ ግጭት መከሰቱን ከአከባቢው ነዋርዎች ለመረዳት ተችለዋል። ነዋሪዎቹ እንደሚሉት ግጭቱ የተከሰተዉ በኦሮሚያ ክልል የቦረና ኦሮሞዎችና በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል በጋር ጎሳዎች መካከል መሆኑን ጠቅሰዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:03

ግጭት በሞያሌ 

በጋርና በቦረና መካካል አልፎ አልፎ ግጭት ይከሰት የነበረ ቢሆንም የአሁኑ ግን በጣም ዘግናኝ መሆኑን በሞያሌ ሆስፒታል የድንገተኛ ቀዶ ሕክምና በለሙያ የሆኑ ግን ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ግለሰብ ይናገራሉ። የድንገተኛ ቀዶ ሕክምና በለሙያ: «ትላንት ከእንቅልፌ እንደተነሳሁ ከጥዋት ወደ 3፤00 ሰዓት አከባቢ ጀምሮ እስከ ምሽት ድረስ ከባድ ተኩስ ነበረ። በማታ እንኳን የቱክስ ድምፅ ስሰማ ነበር። አሁንም ዉጥረት አለ። በዚህ አከባብ መንግስት ርምጃ መዉስድ አቅቶታል። ሰዉ ቀንና ማታ ኢየተፋጀ ነዉ። እኛም ለራሳችን ሕይወት ሰግተናል። ስለዝህ በዚህ ሁኔታ ከቀጠለ በጣም አስቸጋሪ ነዉ። መንግስት ርምጃ ካልወሰደ፤ በጣም የሚዘገንን ሁኔታ ነዉ ኢየሆነ ያለዉ። ኢየሆነ ያለዉ ጥሩ ነገር አይደለም።»

በዚህ ግጭት ሳብያም የሰዉ ሕይወት እንዳለፈና ብዙዎቹም እንደቆሰሉ በሞያሌ ሆስፕታል የድንገተኛ ቀዶ ሕክምና በለሙያዉ ገልጸዋል። ሕይወታቸዉ ያለፈዉ ሰዎች ቁጥር ከአምስት በላይ ነዉ ቢባልም ሌሎችን በማከም ላይ ስለነበሩ የተጎዱትን ለመመዝገብ ግዜዉ አልነበረኝም ይላል። ግን በአይኔ አይቸዋለዉ ያሉትን አጋርተውናል፣ «እኔ በግሌ ሶስት ሰዉ ሕይወታቸዉ ስያልፍ አይቸዋለዉ። ሰባት የሚሆኑ ደግሞ ወደ ተለያዩ ሆስፒታሎች ልከነዋል። ባጠቃላይ ወደ 20 ሰዎች ናቸዉ የቆሰሉት።»
ሌላ የሕክምና ባለሙያ ደግሞ እስካሁን ሕይወታቸዉ ያለፈ እንዲሁም የቆሰሉትን በተመለከተ የምከተለዉን ብለዋል።

ግጭቱን ማን እንደ ጀመረ በግልፅ እንደማይተዋቅ የተናገሩት የድንገተኛ ቀዶ ሕክምና በለሙያ ፣ ሆኖም  የሶማሌ ጎሳ የሆኑት በጋሪዎች መሆናቸው እንደሚወራ ተናግረዋል።  በዚህ ግጭት ዉስጥ የሶማሌ ክልል ልዩ ፖሊስ እጅም አለበት ሲሉ ነዋሪዎች እንደሚናገሩ የኦሮምያ ክልል መገናኛ ብዙሀን በፌስ ቡክ ገጹ ላይ አስታውቋል።

ስለ ግጭቱ መነሻም ሆነ በሰዉና በንብረት ላይ ስለ ደረሰዉ ጉዳት ይህ ዘገባ እስከ ተጠናቀረበት ድረስ ከኦሮምያም ሆነ ከሶሜሌ ክልሎች የወጣ ይፋዊ የሆነ መግለጫ የለም። ዶይቼ ቬሌም በጉዳዩ ላይ የበለጠ መረጃ ለማግኘት ለሁለቱም ክልል የኮሙኒኬሼን ጉዳዮች ሃላፊዎች ተደጋጋሚ የስልክ ጥሪ ቢያደርግም ሊገኙ አልቻሉም። ትላንት ግጭቱ ከተከሰተ በኋላ  የኦሮሚያ ክልል የኮሙኒኬሼን ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ነገሪ ሌንጮ በፌስቡክ ገፃቸዉ ላይ «በሞያሌ በዜጎቻችን ላይ እየደረሰ ያለው ጥቃት ተቀባይነት የለሌውና የሚወገዝ ነው፡፡ ሃላፊነት የተሰጠዉ አካል አስፈላጊውን እርምጃ ወስዶ ጉዳቱን ከወድሁ ማሰቆም አለበት።» ሲሉ አስፍረዋል።

በዛሬዉ እለት የተለያዩ ንግድ ቤቶች እና መኖሪያ ቤቶች ጭምር ተዘግተው መዋላቸውን፤ ሆኖም በመጠኑ የሰዎች እንቅስቃሴ እንዳለና ትናንት ህወታቸዉ ያለፈዉ የሶስቱ ሰዎች የቀብር ስነስረዓት መፈፀሙን የድንገተኛ ቀዶ ሕክምና በለሙያዉ ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል።

ከግጭቱ በኋላ ብዙ ሰዎች ወደ ኬንያ ሞያሌ ኢየተሰደዱ መሆኑን ከሕክምና ባለሙያዎቹ ለማወቅ ተችለዋል። እሄንንም አስመልክቶ ከኬንያ ቀይ መስቀል በኩል መረጃ ለማግኘት ያደርገነዉ ጥረት አልተሳካም።

እንደ ጎርጎረሳዊያኑ አቆጣጠር ከ1994 ዓ/ም ጀምሮ በሞያሌ በቦራናና በጋሪ ጎሳዎች መካከል የወረዳዎች ይገባኛል ጥያቄ መፍትሄ ሳይሰጠዉ ወደ ግጭት ማምራቱን ዘገባዎች ይጠቁማሉ። በ2004 ሕዝባዊ ዉሳኔ ለማድረግ ሙከራ ቢደረግም አለመሳካቱን ዘገባዉ ያትታል።

መርጋ ዮናስ

ሂሩት መለሰ 

Audios and videos on the topic