ግጭትና ዉጊያ ያልራቃት የመን | ዓለም | DW | 15.10.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

ግጭትና ዉጊያ ያልራቃት የመን

በአንድ ሳምንት ዉስጥ ሁለት ጠቅላይ ሚኒስትሮች የተለዋወጡባት የመን ዛሬም የተረጋጋች አትመስልም። ከሰንዓ የሚወጡ የተለያዩ የዜና ወኪሎች ዘገባ እንደሚለዉ በሁቲ አማፅያንና በአልቃይዳ ታጣቂዎች መካከል የተካሄደዉ ዉጊያ ቢያንስ የ12 ሰዎችን ህይወት አጥፍቷል።

እንደዘገባዎቹ በወታደራዊ እንቅስቃሴያቸዉ በሀገሪቱ ማዕከላዊ መንግሥት ላይ ከፍተኛ ጫና ማሳደራቸዉ የሚታየዉ ሁለቱም ታጣቂ ኃይሎች ወደዉጊያ የገቡት የሚቆጣጠሩትን አካባቢ ለማስፋት ባደረጉት ሙከራ ነዉ። በተኩስ ልዉዉጡም ከአማፅያኑ አምስት፤ ከአልቃይዳ ታጣቂዎች ወገን ስድስት መገደላቸዉን ያመለከተዉ ዘገባ ቀሪዎቹ ሲቪሎች መሆናቸዉንም ገልጿል። አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሰኞ ዕለት የተሰየመላት የመን ከሁለት ዓመት ከዘለቀዉ አለመረጋጋት ትላቀቅ ይሆን? ሰንዓ የሚገኘዉን ግሩም ተክለኃይማኖትን በስልክ ስለወቅታዊዉ የየመን ሁኔታ አነጋግሬዋለሁ፤

ግሩም ተክለሃይማኖት

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic