ግጥም፣ የነቃና የታመቀ ስነ-ቃል | ባህል | DW | 20.12.2007
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

ግጥም፣ የነቃና የታመቀ ስነ-ቃል

አጭር ነዉ ይሉታል፣ ምነዋ ቢያጥር፣ ኮረሪማ አይደል፣ ወጥ የሚያሳምር፣ አጭር ነዉ ቁመቱ፣ ብለዉ አሙት አሉ፣ ጠባብ ነዉ ደረቱ፣ ብለዉ አሙት አሉ፣ እንደኔ መች አዩት፣ ቁም ነገሩን ሁሉ! ስትል እንዲት ጎረድረድ ያለች ሴት በቁመቱ አጭር የሆነ ባል በማግባትዋና በባልዋ ቁመት በመታማትዋ የገጠመችዉ ነበር

default

ፍቅር ሞኝ ነዉ አሉ! መቼም ሰዉ ብጤዉን ካገኘ የሚግባባዉ ካጋጣመዉ ያዉ ባገራችን አነገጋገር ኮከቡ ገጥሞአልና አፍንጫ የላትም ፣ቁመና የለዉም የሚባል ነገር የለም ተስማምቶ ተረዳድቶ ተከባብሮ መኖር ነዉ። ይህች ፉንጋ ሴት አጭር ሰዉ አገባች በሚል የሰፈር ሰዉ በማያገባዉ፣ እሷ ፉንጋ፣ ባልዋ አጭር ደሞስ ምኑን ሊወልዱት ይሆን እያለ ሲያማ ሃሜት ዞሮ ዞሮ ከባለቤቱ ጆሮ ይባላል እና፣ ወሪዉ ባለቤቶቹ ጆሮ ደርሶ ባልም መልሱን በግጥም ደረደረ። መልሱን ወደ ኳላ ላይ ያደምጣሉ፣ ግን በአገራችን በግጥም ደስታ፣ ሃሳብ፣ ሃዘን፣ ተስፋ፣ ጥላቻ ይገለጻል። ግጥም የሰዉ ልጅ ሃሳቡን በአመቀ በተቆጠበ ያነጋገር ዘይቤ የሚገልጽበት የቋንቋ ፈጠራ ነዉ። የዛሪዉ የባህል መድረካችን በተለይ በገጠሪቱ ኢትዮጽያ አካባቢ በተለያዩ አጋጣሚዎች የሚሰሙትን የተለያዩ ግጥሞች ከአጭር ወጎቻቸዉ ጋር በማቀናበር ይዞ ቀርቦአል መልካም ቆይታ።