ግድያ እና የተቃውሞ ሰልፍ በኢራን | ዓለም | DW | 28.12.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

ግድያ እና የተቃውሞ ሰልፍ በኢራን

ኢራን ውስጥ የፕሬዝዳንት ማህሙድ አህመዲነጃድን መንግስት በመቃወም ከቅዳሜ አንስቶ በተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ስምንት መድረሱን የኢራን መገናኛ ብዙሀን አስታውቀዋል ።

default

ፖሊስ በርካታ ተቃዋሚዎችንም አስሯል ። የኢራን መንግስት በተቃዋሚ ሰልፈኞች ላይ የወሰደው ግፍ የተሞላበት ዕርምጃ በምዕራባውያን ሀገራት ተወግዟል ። በዓመታዊው የአሹራ በዓል ህዝቡ ለተቃውሞ ሰልፍ አደባባይ የወጣው በዋና ከተማይቱ በቴህራንና እና በሌሎችም ከተሞች ጭምር ነው ። ሂሩት መለሰ ።