ግዙፉ የአሜሪካን የኢንሹራንስ ኩባንያ AIG ቅሌትና ባራክ ኦባማ | ዓለም | DW | 23.03.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

ግዙፉ የአሜሪካን የኢንሹራንስ ኩባንያ AIG ቅሌትና ባራክ ኦባማ

AIG በተባለው ግዙፍ የአሜሪካን የኢንሹራንስ ኩባንያ ውስጥ የተፈጥረው ቅሌት የፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማን አስተዳደርና የሀገሪቱን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማወዛገቡን እንደቀጠለ ነው ።

default

የገንዘብ ሚኒስትር Timothy Geithner

ዓለም ዓቀፉን የገንዘብ ቀውስ ተከትሎ ባጋጠመው ኪሳራ ምክንያት ከመንግስት 180 ቢሊዮን ዶላር ድጎማ የተሰጠው ይኽው ኩባንያ ለተወሰኑ ሀላፊዎች ባከፋፈለው 165 ሚሊዮን ዶላር የጉርሻ ክፍያ ሰበብ መንግስት እየተተቸ ነው ። በተለይ የአሜሪካን የገንዘብ ሚኒስትር ቲመቲ ጌይትነር ሌላው ቢቀር ይህን ያህል ገንዘብ ለሀላፊዎች ሲሰጥ ማስቆም ባለመቻላቸው ከየአቅጣጫው እየተወቀሱ ነው ። ሀያ የአሜሪካን ግዛቶችም በኩባንያው ላይ ክስ ሊመሰርቱበት በዝግጅት ላይ ናቸው ። የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ በበኩላቸው መካሰስና መወቃቀሱን ትተን ምጣኔ ሀብታችንን በማቃናቱ ላይ እናተኩር እያሉ ነው ። አበበ ፈለቀ ከዋሽንግተን

ተዛማጅ ዘገባዎች