1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ግዕዝ በኮንፒዉተር ያስተዋወቁት ኢትዮጵያዊ

ሐሙስ፣ መጋቢት 10 2012

ዶ/ር አበራ የከፍተኛ ትምህርታቸዉን  የተከታተሉት የእንስሳ ሕክምናን ሞያ ነዉ። የግዕዝ ፊደልንና ሥነ ጽሑፍ በኮምፕዩተርና በእጅ ስልክ ውስጥ መጠቀም እንዲቻል አድርገዋል። ዶ/ር አበራ እንደነገሩን በምርምር ባገኝዋቸዉ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎች ሰባት የዩናይትድ እስቴትስና ኢትዮጵያ ፓተንቶች «የባለቤትነት መብትን»ብቻቸውን ይዘዋል።

https://p.dw.com/p/3ZkC9
Älteste äthiopische Bibelhandschrift
ምስል DW/ A.T.Hahn

ግዕዝን በኮምፒዉተር መተየብ የሚያስችል ፈጠራ ባለቤት

በዩናትድ ስቴትስ ኮለራዶ ከተማ ነዋሪ የሆኑት ኢትዮጵያዊዉ ሳይንቲስት ዶ/ር ኣበራ ሞላ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት፣ መናገሻ ኣውራጃ፣ ሰንዳፋ ከተማ መወለዳቸዉን ሲናገሩ በደስታ ነዉ።  በሰሜን አሜሪካ ሲኖሩ ከአራት አስርተ ዓመታት በላይ የሆነቻቸዉ ዶ/ር ኣበራ ሞላ ኮምፕዩተሮችና የእጅ ስልኮች በግዕዝ ፊደል እንዲጽፉ የፈጠሩ ኢትዮጵያዊ ሳይንቲስት ናቸው። ዶ/ር አበራ የከፍተኛ ትምህርታቸዉን  የተከታተሉት የእንስሳ ሕክምናን ሞያ ነዉ። የግዕዝ ፊደልንና ሥነ ጽሑፍ በኮምፕዩተርና በእጅ ስልክ ውስጥ መጠቀም እንዲቻል አድርገዋል። ዶ/ር አበራ እንደነገሩን በምርምር ባገኝዋቸዉ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎች ሰባት የዩናይትድ እስቴትስና ኢትዮጵያ ፓተንቶች ብቻቸውን ይዘዋል። የአክሱም ሓውልት ከሮም ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለስ ብዙ ትግል ያደረጉ መሆናቸዉን ተዘግቦአል። በእዚህ ቅንብር  ዶ/ር ኣበራ ሞላን በቅድምያ ግዕዝን በኮምፒዉተር መተየብ ስለሚያስችል ፈጠራ ዉጤታቸዉ ጠይቀናቸዋል።

አዜብ ታደሰ 

እሸቴ በቀለ