ግንባታቸው የተጓተተው የእስቴ መስጊዶች | ኢትዮጵያ | DW | 05.06.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ግንባታቸው የተጓተተው የእስቴ መስጊዶች

በዓመቱ አጋማሽ በመካነ ኢየሱስ ከተማ የተቃጠሉ መስጊዶችን መልሶ ለመገንባት የገንዘብ እጥረት እንዳጋጠመው የመስጊድ አሰሪ ኮሚቴ አመለከተ፡፡ በደቡብ ጎንደር ዞን እስቴ ወረዳ መካነ ኢየሱስ ከተማ ጥር 26/ 2011 ዓ.ም በአካባቢው ተፈጥሮ በነበረው አለመረጋጋት በከተማው የሚገኙ የተለያዩ የአገልግሎት መስጫ ተቋማትና መስጊዶች መቃጠላቸው ይታወሳል፡፡

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:42

«ለግንባታው ቃል የተገባው ገንዘብ አልተሟላም»

መስጊዶችን ለመገንባት የተለያዩ ጥረቶች እተደረጉ ቢሆንም በገንዘብ እጥረት የቤተእምነቶቹ ግንባታ መጓተቱን በመካነ ኢየሱስ ከተማ የ03 ቀበሌ መስጊድ አሰሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ ሐጂ ኡስማን አሊ ኢብራሂም ለዶይቼ ቬለ DW በስልክ ተናግረዋል፡፡

ሀጂ ኡስማን እንደሚሉት መስጊዶችን መልሶ ለመገንባት 8 ሚሊዮን ብር የሚያስፈልግ ቢሆንም አስካሁን የተሰበሰበው ግን ከአንድ ሚሊዮን ሚበልጥ ኤደለም፡፡ ለተለያዩ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን  ጭምር እገዛው እንዲደረግ መልዕክት ማስተላለፋቸውን የሚናገሩት ሀጂ ኡስማን አሁንም መላው ኢትዮጵያውያንና በውጪ የሚኖሩ ወገኖች እጃቸውን ለእርዳታ እንዲዘረጉ ጠይቀዋል፡፡ የአማራ ክልል እስልምና ጉዳች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕረዚደንት ሀጂ ሰኢድ ሙሐመድ በበኩላቸው ባለፈው ዓመት በተለያዩ አካባቢዎች በተፈጠሩ ግጭቶች አብያተ ክርስቲያናትና መስጊዶች መቃጠላቸውን አስታውሰው በወቅቱ ቤተ እምነቶቹን መልሶ ለመገንባት የነበረው ግለት መቀዛቀዙን ይናገራሉ፡፡

በወቅቱ በነበረ አለመረጋጋት በከተማዋ ተቃጥለው የነበሩ መስጊዶች ግንባታቸው የተጀመረ ቢሆንም በገንዘብ እጥረት የተፈለገውን ያህል መሄድ አለመቻሉን ሀጂ ሰኢድ አመልክተው ኅብረተሰቡ ድጋፍ እንዲደያርግ ጥሪ አቅርበዋል። የአሰሪ ኮሚቴው ሰብሳቢ ሀጂ ኡስማን ኢብራሂም አሊ እንዳገለፁት በአካባቢው ህብረተሰብ ዳጋፍ የመስጊዶቹ የመሰረት ግንባታ ተጀምሯል። ኅብረተሰቡም የሚያደርገውን የቁሳቁስ፣ የጉልበትና የገንዘብ ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበል። በቀጣይ ወንድማማችነትን በማጠናከር ሰላምን በዘላቂነት ለማስፈን ሙስሊሙ  ኅብረተሰብ የላቀ ድርሻ አንዲወጣ ደግሞ አቶ ጀማል ሙሃመድ የተባሉ የባሕር ዳር ከተማ ነዋሪ ተናግረዋል። ዝርዝሩን ከባሕር ዳር ዘጋቢያችን ዓለምነው መኮንን ልኮልናል።

ዓለምነው መኮንን

ሸዋዬ ለገሠ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

Audios and videos on the topic