ግብፅ ወዴት እያመራች ይሆን ? | ዓለም | DW | 03.02.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

ግብፅ ወዴት እያመራች ይሆን ?

ሙስና ጭቆና እና የኑሮ ውድነት የወለደው የግብፅ ህዝባዊ አመፅ ከትናንት አንስቶ አዲስ መልክ ይዟል ።

default

የማታው ብጥብጥ በከፊል

ከሥልጣን እንዲወርዱ የተጠየቁት የግብፁ ፕሬዝዳንት ሆስኒ ሙባረክ ፣ አስተዳደራቸው ያንገፈገፈው ህዝብና ተቃዋሚዎች እንደፈለጉት በአስቸኳይ እንደማይሰናበቱ ባሳወቁ በማግስቱ ትናንት በደጋፊዎቻቸውና በተቃዋሚዎች መካከል የተቀሰቀሰው ግጭት ዛሬም አልበረደም ።ከቱኒዚያ ወደ ግብፅ የተዛመተው አመፅ እስራኤልን ጨምሮ ሌሎች የመካከለኛው ምስራቅ አገራትን እንዳሰጋ ነው ። እንደ እስራኤል ያሉ መንግስታት የአሁኑ አካሄድ ግብፅ በአክራሪ ሙስሊምች እጅ እንድትወድቅ ሊያደርግ ይችላል እያሉ ነው ። በነዚህ ወገኖች እምነት አመፁ የኢራኑን አብዮት ዓይነት ውጤት ሊያስከትልም ይችላል ። እዚህ ጀርመን በሚገኘው በ Munster ዩኒቨርስቲ የአረብ ባህል እና የእስልምና ሃይማኖት ጥናት ተቋም ሃላፊ ቶማስ ባወር ግን የተለየ አስተያየት ነው ያላቸው ።
Dossierbild 2 Tahrir Square Proteste in Ägypten

ሰልፈኞች ጎራ ለይተው ሲጋጩ

ግብፅ ወዴት እያመራች ይሆን ? የግብፅ ዜጎችን ብቻ ሳይሆን መላውን ዓለም ማነጋገር የያዘ ዐብይ ጥያቄ ነው ። የሙባረክ ዕጣ ፈንታ በእጅ ወድቋል የሚባለው የግብፅ ወታደር እስካሁን ህዝቡን አልነካም ። ሙባረክንም መደገፉንና መጠበቁንም አልተወም ። አመፁ መንስኤ ሆኖ ሙባረክ የሾሟቸውን አዲስ ምክትል ፕሬዝዳንት ኦማር ሱሌይማንን ህዝቡ አልተቀበለም ። ምናልባትም ወታደሩ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዥር ሹሙን ሳሚ ኤናንን ወደ ሥልጣን ሊያመጣቸው ይችል ይሆናልም ይባላል ። ወታደሩ ሥልጣን ካልያዘ ደግሞ ወደ ሥልጣን ሊጠጋ የሚችል ጠንካራ የተደራጀ ኃይል ማን ሊሆን ይችላል የሚለውም እያነጋገረ ነው ።

Entwicklung der Unruhen in Ägypten Flash-Galerie

ሞሀመድ ኤል ባራዳይ

እስካሁን በተሻለ ሁኔታ የተደራጀው ፣ በመንግስት የታገደው የሙስሊም ወንድማማቾች ንቅናቄ ነው ። ይህ ቡድን አሁን የተፈጠረውን የፖለቲካ ክፍተት ለሸፍን ይችላል ሲሉ አንዳንድ የፖለቲካ ተንታኞች ይናገራሉ ። ሥልጣን የመያዝ ፍላጎት ያላሳየው ወይም ደግሞ ጣልቃ መግባት ያልፈለገው የሙስሊም ወንድማማቾች ንቅናቄ ግን በምዕራቡ ዓለም በአክራሪነትና በአደገኝነት ይፈረጃል ። የዚህ ቡድን ወደ ሥልጣን መጠጋት ግብፅን በአክራሪ ሙስሊሞች እጅ ያስገባል የሚል ስጋትም አሳድሯል ። በጀርመኑ ሙንስተር ዩኒቨርስቲ ስር የሚገኘው የአረብ ባህልና የእስልምና ሃይማኖት ጥናት ተቋም ሀላፊ ቶማስ ባወር ግን ይህ የተሳሳተ አመለካከት ነው ይላሉ ። « ምን ማለት እንደሚቻል ይከብዳል ። በአሁኑ ጊዜ በምዕራቡ ዓለም በተደጋጋሚ ከአክራሪ ሙስሊሞች በኩል አደጋ ይደርሳል ተብሎ የሚቀርበው ዘገባ ያሳዝነኛል ። ሁሉም የፖለቲካ ኃይሎች እንዲሁ ከእስልምና ጋር የጠበቀ ግንኙነት ያላቸው አለመሆኑ ነው መታየት ያለበት ። አጠቃሎ በጅምላ ሁሉንም ከእስልምና ጋር የተቆራኙ አድርጎ ማቅረቡ ወደ አሸባሪነት ማስጠጋት ይሆናል ። የሙስሊም ወንድማማቾች ማሕበር በዲሞክራሲው ሂደት እንደሚሳተፍ በግልፅ አስታውቋል ። እርግጥ ነው ከመካከላቸው የተለያዩ አቋም ያላቸው እንዳሉ የታወቀ ነው ። በአጠቃላይ ሲታይ ንቅናቄው ለዲሞክራሲያዊ ስርዓት መመስረት የሚያሰጋ አይደለም ። »

Ägypten Kairo Proteste

ድንጋይ ውረራ

የሙስሊም ወንድማማቾች ንቅናቄ ከ 20 እስከ 40 በመቶ የሚደርስ የህዝብ ድጋፍ አለው ። አመፁ እንደተጀመረ ወደ ግብፅ ለተመለሱት ለኖቤል የሰላም ተሻለሚው ለሞሀመድ ኤል ባራዳይ ድጋፍ ሰጥቷል ። የግብፁ ህዝባዊ ንቅናቄ የመከከለኛው ምስራቅ አገራት በተለይ ደግሞ እንደ እስራኤል ያሉ መንግስታትን የሚያሳስብ መሆኑ አልቀረም ። እስራኤል ገና ከመነሻው የግብፁ አመፅ የኢራኑ አብዮት ያመጣውን ውጤት በግብፅም ማስከተሉ አይቀርም እያለች ነው ። እንደ ቶማስ ባወር ይህም የሚሆን አይደለም ። « እንደሚመስለኝ ይሄ ፕሮፖጋንዳ ነው ። የኢራኑ እስላማዊ አብዮት መሪ አያቶላ ሆሚኒ ከፓሪስ ተነስተው ቴህራን በመግባት ሥልጣን እንደያዙት ወደ ግብፀ በመጓዝ ሥልጣን የሚጨብጥ ኃይል እንደሌለ እስራኤሎች ጠንቅቀው ያውቁታል ። ይህን ፍፁም ሊንቀሳቀስ ካልቻለው የሰላም ሂደት ጋር አያይዘው መመልከት የለባቸውም ። ይሄ ፣ ባለበት የቆመው የሰላም ድርድር ምንም እንኳን ክሊንተን ይሳካል ብለው በብሩህ ዓይን ቢመለከቱትምና ፍልስጤማውያንም ለዚሁ የማይቻል እስከመሰለው ድረስ ዝግጁነታቸውን በጥሞና ቢያሳዩም እስራኤል አንድ አፅቅ እንኳን ፈቀቅ አላለችም ። የአሁኑ የእስራኤል የቀኝ አክራሪ መንግስት የሚፈልገው ይሄን አቋሙን የሚቀበሉለትን የጎረቤት አገራት ነው ። ሙባራክ ደግሞ የነሱ ትዕዛዝ ተቀባይና አስፈፃሚ ነበሩ ። በሙባረክ ደጋፊዎችና ተቃዋሚዎች መካከል የተቀሰቀሰው ግጭት ዛሬም በአስከፊ ሁኔታ ቀጥሏል ። ዲርክ ቶማስ ባወር እንደሚሉት በዓይነቱ የሚለየው የግብፅ ችግር በጥንቃቄ ካልተያዘ መዘዙ የከፋ መሆኑ አይቀርም ። «ብዙዎቹ የመካከለኛው ምስራቅ ጉዳይ የሚለከታቸው ወገኖች ስሜታዊነት ይንፀባረቅባቸዋል ። ይሄ ለውጥ እንዳይደረግ በጠጣር መንገድ የተጓዙት የአረብ አገሮች ሁሉ እየተቀጡ ናቸው ። የተጠራቀመው አቧራ ቱኒዝያውያን ጠርገውት ፍፃሜ እስኪያገኝ ድረስ እንደተቆለለ ነበር ። አሁንም ቢሆን ይሄ ስሜታዊነት እንደተንሰራፋ ነውና ሰዉ መጠንቀቅ አለበት ። መጠኑን አልፎ እንዳይሄድ መጠንቀቅ አለበት ። » ሂሩት መለሰ ነጋሽ መሀመድ