ግብፅ ኢትዮጵያንና ሱዳንን ለሦስትዮሹ ዉይይት መጋበዟ | ኢትዮጵያ | DW | 06.01.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ግብፅ ኢትዮጵያንና ሱዳንን ለሦስትዮሹ ዉይይት መጋበዟ

በዚህ ሳምንት መጀመርያ ላይ የግብፅ ዉጭ ጉዳይ ምንስትር የኢትዮጵያና የሱዳን  አቻዎቻቸዉን የአባይ ዉሃ አጠቃቀም በተመለከተ ለመወያየት ለሶስትዮሹ ስብስባ መጋበዛቸዉን የግብፅ ዉጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃላቀባይ ለዶቼ ቬሌ ተናገርዋል።  

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:06
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
03:06 ደቂቃ

የሶስትዮሹ ዉይይት

ቃላቀባዩ አህሜድ አቡዛይድ ስብሰባዉ በሱዳን ዋና ከተማ በካርቱም ሊሆን እንደሚችል ጠቅሰዉ ግን የተቆረጠለት ቀን እንደሌለ ይናገራሉ።

ሶስቱም አገሮች የመግባቢያ ሰነድ (declaration of principles) ከተፈራረሙ በኋላ በ«ሕዳሴ ግድብ» ግንባታ ላይ መስማመት መቻላቸዉን ዘገባዎች ይጠቁማሉ። ከስምምነቱም በኋላ ሶስቱም አጋሮች ግድቡ የሚያመጣዉን ተፅዕኖ በተመለከተ የቴክኒክ ጥናት እንዲደረግ ወስነዋል።

በፊት የሶስቱ አገራት የዉጭ ጉዳይ ምንስትሮች በየጊዜዉ  እየተገናኙ ኢትዮጵያ ሥለምትገነባዉ  ግድብ» ሲወያዩ እንደነበር የግብፅ ዉጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃላቀባይ አህመድ ገልፀዉ አሁን በግብጽ በኩል የተደረገዉ የዉይይት ግብዣ ዋና አላማን በተመለከተ እንዲህ ይላሉ፣ «በፊት የነበሩት ስብሰባዎች ዋና ዓለማ የነበረዉ ለሶስቱም አጋሮች የዉሃ ሃብት ምንስትሮች የቴክንክ ዉይይት ሲያደርጉ የፖለትካ ድጋፍ ለመስጠት ነበር። ሁሌም ይህን የቴክንክ ዉይይት በተከታታይ ማድረግ አስፈላጊ ነዉ። ይህም የትብብርና የጋራ ተጠቃሚነት እንዲኖርና ሶስቱንም አገሮች የማይጎዳ አላማ ተፈፃምነት እንዲያገኘ ይሄዳል። የሶስቱ አጋሮች የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች  ሳይነጋገሩ ጥቂት ወራቶችን አስቆጥረዋል። ስለዚህም ነዉ የግብፅ መንግስት የሶስቱም የዉጭ ጉዳዮች ምንስትሮች ዳግም ተሰብስበዉ የፖለትካ ድጋፋቸዉን እንደሰጡ ተገቢ ሆኖ ያገኘችዉ።»


ባለፈዉ መስከረም  ግድቡ ሊያመጣ የሚችለዉን ተፅኖ መተመለከተ ሁለት የፋረንሳይ ኩባኒያዎች፣ ማለትም BRLi እና Artelia የተባሉት የቴክንክ ጥናት እንድያካሄዱ ስወስቱ ሐገራት ተስማምተዋል። ሁለቱም  ኩባኒያዎች ጥር ወር መጨረሻ ስራቸዉን እንደሚጀምሩም ቃል አቀባዩ አህመድ ይናገራሉ።

ቀደም ሲል የኢትዮጵያ መንግስት የጥናቱ ዉጤት የግንባታዉን ሒደት እንደማይለውጥ ገልጦ ነበር። ይህን የእትዮጵያ መንግስትን አቋም እንዴት ይመለከቱታል ለሚለዉ ጥቃቄ ቃል አቀባዩ የሚከተለዉን መልስ ሰጥተዋል። «እንግዲህ ዋናዉ የስምምነቱ ማዕቀፍ በ2007 በኢትዮጵያ፣ በግብፅና ሱዳን መካከል የተደረገዉ የመግባቢያ  ስምምነት ነዉ። በዝህ ስምምነትም ሶስቱም አገሮች የተስማሙት በየደረጃዉ የሚደረገዉ የፕሮጄክቱ ሒደት የሚያመጣዉን የጥናቱን ዉጤት እንደምያከብሩ ነዉ። ስለዚህ የጥናቱ ዉጤትና እንዴት ሊፈፀም ይችላል የሚለዉ እስካሁን ማጣቀሻ ነጥባችን ነዉ።»


የግብፅ መንግስትን የዉይይት ግብዣን በተመለከተ የኢትዮጵያ መንግስት ባለሥልጣናት ሥለሚኖራቸዉ አቋም እንዲያስረዱን ያደረግነዉ ጥረት አልተሳካም።

    
አሁን ግብፅ ኢትዮጵያንና ሱዳንን ለዉይይት መጋበዟን እንዴት ይመለከታሉ ብለን የፌስቡክ ተከታታዮቻችንን ጠይቀን ነበር። አስተያየታቸዉን ከሰጡት መካከል  «ይሄ እኮ የታወቀ ነው፣ ለጉርብትናው እንጂ የአባይ ጉዳይ የእኛ እና የኛ ውሳኔ ነው፣ እንደፈለግን የማድረግም መብት አለን። የግብፅም ሆነ የሱዳን ፍቃድ አያስፈልገንም» ያሉ አሉ። ሌሎች ደግሞ ግብፆች «የማያዋጣቸው መሆኑን አሁን  የተገነዘቡት ይመስለኛል አሁን ወደ ድርድር የመጡት» ሲሉ አስተያየታቸዉን ሰጥተዉናል።

መርጋ ዮናስ

ነጋሽ መሃመድ 


 

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች