ግብፅና አፍሪቃ ኅብረት | አፍሪቃ | DW | 22.07.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

ግብፅና አፍሪቃ ኅብረት

የአፍሪቃ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ዶክተር እንኮሳዛና ድላሚኒ ዙማ፤በዛሬው ዕለት የግብዕን ጊዜያዊ መንግሥት ልዩ መልእክተኛ አምባሳደር ሞና ኦማርን አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኘው የኅብረቱ ዋና ጽ/ቤት ተቀብለው ማነጋገራቸው ተመለከተ።

African Commision President Nkosazana Dlamini-Zuma (2L) speaks during the openning of the sixth meeting of the finance and economy ministers and the African Union Development Planning in Abidjan on March 25, 2013. A FP PHOTO / ISSOUF SANOGO (Photo credit should read ISSOUF SANOGO/AFP/Getty Images)

ዶክተር እንኮሳዛና ድላሚኒ ዙማ

ከአፍሪቃ አንድነ ት ድርጅት (አፍሪቃ ኅብረት) መሥራች አባል ሃገራት አንዷ፣ ግብፅ ፣ በቅርቡ በህዝብ ተመርጠው የነበሩት ፕሬዚዳንቷ ሙሐመድ ሙርሲ ከሥልጣን እንዲወገዱ በተደረገበት እርምጃ ሳቢያ ፤ ግብፅ ባለፈው ሰኔ 28 ቀን 2005 ዓ ም፤ለጊዜው መታገዷ ተገቢ አይደለም ሲሉ የግብፅ ተወካይ ሞና ኦማር ገለጡ። የአፍሪቃ ኅብረት ያቋቋመው ቡድን የግብጽን ተጨባጫ ሁኔታ አጥንቶ ካቀረበ በኋላ ውሳኔው እንደገና እንደሚመረመር ድላሚና ዙማ ገልጸዋል። የግብፅ ልዩ ልዑክና ድላሚና ዙማ፤ ከተወያዩ በኋላ በከፈፍተና ደረጃ የተዋቀረ የአፍሪ ኅብረት አጥኚ ቡድን ወደ ግብፅ በመጓዝ፤ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ወገኖች ሁሉ ጋ ተገናኝቶ ከተነጋገረ በኋላ ተመልሶ ስለተልእኮው ለአፍሪቃ ኅብረት የሰላምና ፀጥታ ም/ቤት ዘገባውን እንዲያቀርብ ተስማምተዋል።
የግብፅ ተወካይ ሞና ኦማር---
«የወቅቱን የግብፅ ሁኔታ በተመለከተ የአፍሪቃ ኅብረት የሰላምና የፀጥታ ም/ቤት የወሰደው እርምጃ አሳስቦናል ፣ አሳዝኖናል። ምክንያቱም ስለተጨባጩ የግብፅ ይዞታ ግንዛቤ የማጣት ችግር አጋጥሞአልና!እዚህ የመጣነው፤ በቅርቡ የተካሄደው አብዮት የህዝባዊ መነሣሣት ውጤት እንጂ፤ ህገ-ወጥ የህገ -መንግሥት ለውጥ እንዳይደለ ለማስረዳት ነው።»
የአፍሪቃ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ፤ ተከታዩን ምላሽም ሆነ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
«አጥኚው ቡድን ሳይመለስ ውሳኔ ማሳለፍ አንችልም። አጥኚው ቡድን ለሰላምና ፀጥታው ም/ቤትዘገባውን ያቀርባል። ምክንያቱም የሰላምና ጸጥታው ም/ቤት ነውና መጀመሪያውንም አጥኚው ቡድን እንዲቋቋም ያደረገው። ቡድኑ የጥናት ውጤቱን ሲያቀርብ ያን መነሻ በማድረግ ተገቢ የሆነውን እርምጃ እንወስዳለን።»

ተክሌ የኋላ

አዜብ ታደሰ

አርያም ተክሌ