ግብጽ-ጋዜጠኞች ላይ የሚደረግ አፈና | አፍሪቃ | DW | 01.10.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

ግብጽ-ጋዜጠኞች ላይ የሚደረግ አፈና

በጎ አ 2011 ዓ,ም በግብፅ የተቀጣጠለ አብዮት፤ ዋና ዓላማ በሲቢሉ ላይ የሚደረገዉን ወታደራዊ እርምጃ ለማስቆም ነበር። ነገር ግን ከሁለት ዓመት ከመንፈቅ በኋላ ዛሪም፤ ወታደሩ በሲቢሉ ላይ የሚያካሂደዉ የሃይል እርምጃ እንደቀጠለ ነዉ። የሰላ ብዕር የያዙ ጋዜጠኞችም፤ ሥራቸዉን እንዳይሰሩ ይታፈናሉ።

የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች፤ በበኩላቸዉ እንዲህ አይነቱን አካሄድ ለማስቀረት፤ በሀገሪቱ አዲስ ሕገ-መንግስት ላይ በማፅደቅ ለማስቀረት ይፈልጋሉ። ካይሮ ከተማ ስትወሳ፤ ጉጉት እና ጥሩ የመረጃ ትስስር ያለባት፤ እና የሁሉ ነገር መጀመርያ ተደርጋ ትታሰባለች።

በራሃማዋ የሲናይ ደሴት ሰዎችን ስለማዘዋወር ወንጀል በፃፈዉ ዘገባዉ ባለፈዉ ዓመት «ሳሚር ካዚር» የተሰኘዉን የግብፅ ሽልማት ያገኘዉ የ38 ዓመቱ ግብጻዊ ጋዜጠኛ የአህመድ አቡ ዴራ፤ የሥራ ባልደረቦች፤ የሙገሳ መዝሙር ይዘምሩለታል። ሞሃመድ አቡ አድሃም፤ የአቡዴራ የረጅም ግዜ ሠራተኛ ነዉ።

«አህመድ አቡዴራ ለሚያገኛቸዉ መረጃዎች ሁሉ፤ ከዋና ምንጩ ማረጋገጫን ማግኘት ይፈልጋል። አቡ ዴራ አንድ የተረጋገጠ መረጃን ለማግኘት፤ በቅድምያ ብዙ ነገሮችን በመጠየቅና ማስተያየት ይጠቀማል። ምንናልባትይህን የሚያደርገዉ ፤ እሱ እራሱ አርብቶ አድር ቤተሰቦች ስለነበሩት ይሆናል»
ለግብጽ ወታደር አቡ ዴራ ወንጀለኛ ነዉ። ምክንያቱም የተከለከሉ የወታደራዊ ተቋሞችን በፊልም ቀርፆአል፤ ከዝያም በላይ የግብፅ ወታደር ሲናይ በረሃ ላይ ጀሃዲስቶችን ለማደን በጣለዉ ጥቃት በስህተት አንድ መስጂድን እና አንድ የመኖርያ ቤትን መቶአል የሚል ከእዉነት የራቀ ዜናን አሰራጭቶአል በሚል ነዉ። አቡ ዴራ ለዚህ ዘገባዉ በወታደራዊዉ ፍርድ ቤት እንዲቀርብ ተደርጎአል። ይህ ከትናንት በስትያ በግብጹ ወታደራዊዉ ፍርድ ቤት የጀመረዉ ችሎት፤ ለሚቀጥለዉ ሳምንት ቀነ ቀጠሮ ተይዞለታል። ፍርድ ቤቱ አቡ ዴራን ጥፋተኛ ብሎ ከበየነበት የእድሜ ልክ እስራት እንደሚጠብቀዉ ተነግሮአል።
የአቡ ዴራ፤ ክስ፤ የፕሪስ ነፃነት እንዲሁም ማንኛዉም ሲቪል ህብረተሰብ፤ በወታደራዊ ፍርድ ቤት እንዳይዳኝ የሚለዉን የግብፅ ህዝብ ሁለት ዋና ጥያቄን በማንሳቱ፤ በሀገሪቱ ከፍተኛ ቀልብን ስቦ እያነጋገረ ነዉ። እነዚህ ሁለቱ ነጥቦች የግብጽ ህዝብ፤ የሆስኒ ሞባረክ መንግስትን በመቃወም ለአብዮት ያነሳሳዉ ዋና ጥያቄዎቹ ነበሩ። ከሁለት ዓመት ከመንፈቅ በኋላ ዛሪም ታድያ ይህ ጥያቄ መልስን አላገኘም።

የግብፁ ህዝባዊ አብዮት ለአጭር ግዜ በማበብ ፤ የሙባረክን መንግስት ገርስሶና፤ በሀገሪቱ ለአጭር ግዜ ነጻ ሚዲያን አጎናፅፎ፤ በጎአ 2012 ዓ,ም ፕሬዚዳንት ሙርሲ ስልጣንን ሲቆናጠጡ መክሰሙ ይታወቃል።

በተለይ የቀድሞዉን የግብፅ ፕሬዚዳንት ሙርሲን ከሥልጣን መነሳት ተከትሎ፤ በሲና በረሃ፤ በፀጥታ አስከባሪዎች እና ጀሃዲስቶች መካከል ያለዉ ደም አፋሳሽ ዉጥረት መሃል የሚገኙ ጋዜጠኞች፤ ሁኔታ እጅግ የከፋ አድርጎታል። በሰሜናዊ ሲና በረሃ የጋዜጠኞች ማህበር ሊቀመንበር አብዱል ካድር ሙባረክ እንደሚሉት ጋዜጠኞች ይታፈናሉ፤

*** VERWENDUNG NUR BERICHTERSTATTUNG MEDIENPREIS ENTWICKLUNGSPOLITIK *** Portrait Journalist Ahmad Abu Dirah aus Ägypten, Teilnehmer des Deutschen Medienpreis Entwicklungspolitik 2013, Finalist Region Nah-/ Mittelost. Bild aus dem Privatarchiv, Undatierte Aufnahme

ጋዜጠኛ አህመድ አቡ ዴራ

« እዚህ የሚሠሩ ጋዜጠኞች ተለጉመዉ ነዉ ሥራቸዉን የሚያከናዉኑት። በተጨማሪ አካባቢዉ ላይ ለጋዜጠኞች በቂ የደህንነት ጥበቃ ያለ አይመስለኝም። ብዙ መከራን መሸከም ተገደናል። ገና ለገና በፀጥታ አስከባሪዎች ተያዝን አልተያዝን፤ በታጣቂዎች ተገድልን አልተገደልን ብለን በፍርሃት ነዉ የምንኖረዉ»

አብዱል ካድር ሙባረክ፤ ጋዜጠኞች ላይ ይደረጋል ያሉት የአፍ ልጓም፤ እንደ ግብፅ ጀነራሎች ፍላጎት እንደተፈለገዉ አሁንም ጥብቅ አይደለም። ለዚህም ነዉ ትናንት የግብፅ ወታደር ቃል አቀባይ፤ በሚዲያ ላይ በቀጣይ አንዳንድ እቀባ እንደሚያደርግ ይፋ ያደረጉት። እንደ ቃል አቀባዩ ወደ ፊት ስለ ግብፅ ወታደር በሚዲያ ላይ ይፋ የሚሆን ዘገባ ሁሉ፤ በቅድምያ ከወታደራዊዉ ሃይል ይሁንታን ማግኘት ይኖርበታል። እንደ ግብፅ ወታደር፤ የብሄራዊ የፀጥታ ጉዳይን በተመለከተ፤ በሁሉም በኩል ሃላፊነትን መዉሰድ ይጠይቃል። ይህ አዲስ ህግ ታድያ በሲና ለሚገኙት ጋዜጠኞች አመቺ ነገርን አልያዘም። ጋዜጠኛ አቡ በከር አድሃም ቅሪታዉን እንዲህ ይገልፃል፤

«እኛ በሲና የምንገኝ ጋዜጠኞች፤ ህይወታችንን እንደፈለግን አይደለም የምንመራዉ፤ ጠዋት ለሥራ ከቤቴ ስወጣ፤ ባለቤቴን በትክክል የማስረዳት፤ ምናልባትም ተመልሼ እንደማልመጣ ነዉ። ምናልባት ፀጥታ አስከባሪዎች ሊያስሩኝ ይችላሉ፤ አልያም የአሸባሪዎች ጥይት ሊያገኝኝ ይችላል እላታለሁ»

መሃመድ ሙርሲ ከስልጣን ከተወገዱ ወዲህ የወጣዉ የሰዓት እላፊ ደንብ፤ በተለይ የፕሪስ ሰራተኞችን ስራ እጅግ አክብዶታል። የፀጥታ ሃይሎች ጋዜጠኞችን እና ማንኛዉም አይነት ሃያሲ ማሰር ይችላሉ፤ ከዝያም ባለፈ የክስ አንቀጸን ይዘዉ ወታደራዊዉ ፍርድ ቤት ማቆም ይችላሉ።
የግብጽ ግዚያዊ መንግሥት ሲቢሎች በወታደራዊ ፍርድ ቤት እንዳይዳኙ መፈለጉን ይገልፃል። ይህን በተመለከተ የግብጹ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ናቢል ፋሚ ባለፈዉ ሳምንት በኒዮርኩ የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር አረጋግጠዋል። በሀገሪቱ የሚገኙ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ለዚህ ጉዳይ ጥሩ አጋጣሚን አግኝተዋል። በግብፅ የሚገኘዉ የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅት ዋና ተጠሪ ሃፊዝ አቡ ሳዳ እንደሚሉት፤

«አሁን ይህን ርዕስ ልናነሳ የምንችልበት ጥሩ አጋጣሚ ነዉ። ምናልባትም ይህን አጋጣሚ ካልተጠቀምን፤ ሁኔታዉ በምንም አይነት ሊቀየር አይችልም። ይህ ማለት ደሞ በቀጣይ ሲቢሎች ወታደራዊዉ ፍርድ ቤት ሲዳኙ እናያለን»እንደ አቡ ሳይዳ ወደፊት ከወታደራዊዉ ሃይል ገና ከባድ ትግል ይገጥማል። በአሁኑ ሰዓት ወታደሩ ሃይል ተቀባይነት ስላለዉ ትግሉ ከባድ ሊሆን ይችላል።በሀገሪቷ ወደፊት ለሚቀርበዉ የመጀመርያዉ የህገ መንግሥት ረቂቅ ላይ ሲቢሎች ከወታደራዊዉ ፍርድ ቤት እዳይቀርቡ ይደነግጋል። እንዲያም ሆኖ በህገ መንግሥቱ ረቂቅ አንቀጽ 174 ላይ እንደተቀመጠዉ፤ ወንጀለኛዉ በወታደራዊ ሃይል ላይ ቀጥታ ወንጀል ከፈፀመ ግን በወታደራዊዉ ፍርድ ቤት እንዲዳኝ ይደነግጋል።

አዜብ ታደሰ

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic