ግብረ ሰናይ ሰራተኞች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት በሶማሊያ | የሶማልያ ውዝግብ | DW | 20.10.2008
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

የሶማልያ ውዝግብ

ግብረ ሰናይ ሰራተኞች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት በሶማሊያ

ባሳለፍነዉ ሳምንት በሶማሊያ በተከታታይ የተሰነዘሩት ጥቃቶች ሁለት የግብረ ሰናይ ባልደረቦችን ህይቀት ቀጥፈዋል።

ተሰዉሮ ጥቃት ማድረሱ ተለምዷል

ተሰዉሮ ጥቃት ማድረሱ ተለምዷል

የተመድ የዓለም የምግብ ድርጅት WFP ባልደረባ ባለፈዉ ዓርብ ሲገደል እሁድ ዕለት ደግሞ የመንግስታቱ የህፃናት መርጃ ድርጅት UNICEF አንድ አባሉን በተመሳሳይ ድርጊት ማጣቱ ተሰምቷል። ጽሕፈት ቤቱ ኬንያ ዋና መዲና ናይሮቢ የሚገኘዉ UNICEF SOMALIA ግድያዉን እያጣራ መሆኑን ገልጿል። የሶማሊያ ዳግም ነፃ አዉጪ ግንባር ግድያዉን አዉግዞ የዉጪ ወራሪዎች በአገሪቱ መገኘታቸዉን ለድርጊቱ ተጠያቂ አድርጓል።