ግቤ ሦስት ግንባታ እና ተቃዉሞው  | ኢትዮጵያ | DW | 28.12.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ግቤ ሦስት ግንባታ እና ተቃዉሞው 

1, 870 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ሃይል የማመንጨት አቅም ያለዉ የግልገል ግቤ ግድብ ባለፈዉ ቅዳሜ ተመርቋል። ይህ የኃይል ማመንጫ ግድብ በወንዙ የፍሰት መጠን እና በአካባቢዉ የሚኖሩ ሰዎች ላይ ተፅዕኖ እንደሚኖረዉ ሳርቫይቫል እንቴርናሽናል ሲገለፁ ቆይቷል። የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ዘመቻዉን«መሰረተ ቢስ»  ይላሉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:53
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
03:53 ደቂቃ

ግድቡ ላይ የሚቀርበዉ ትችት

በደቡብ ክልል በኦሞ ወንዝ ላይ የተገነባዉ የግልጌል ግቤ ሶስት ግድብ 246 ሜትር ከፍታና 610 ሜትር ስፋት እንዳለዉ ተጠቅሰዋል። ግድቡ በኦሞ ወንዝ አከባቢ ያሉትን ገበሬዎችና በአከባብዉ ተፈጥሮ ላይ ተፅኖ ይኖረዋል በማለት 400 ድርጅቶች ግድቡን በመቃወም ፊርማ አሰባስበዋል።  የቀድሞ የኢትዮጵያ  ጠቅላይ ሚንትር መለስ ዜናዊ ግልገል ግቤ ሶስትን በተመለከተ ሳርቫይቫል እንቴርናሽናልና የመሳሰሉት የመብት ተሟጋቾች አጄንዳ አድርገዉ መነሳታቸዉን አከባቢዉ «ሙዚየም» ሆኖ እንዲ ቀጥል «ቢራብሮ እንዳይረበሽ በሚል ጥያቄ የሚያነሱ» ሲሉ ተችተዋዉ ነበር።

አሁን ደግሞ የኢትዮጵያ ኤሌክትርክ ሃይል የህዝብ ግኑኝነት ዳይሬክተር አቶ  ምስክር ነጋሽ፣ «መሰረተ ቢስ አሉባልት» ይላሉ።

የአናሳ ጎሳ መብት ተከራካሪዉ ሳርቫይቫል ኢንቴርናሽናል የተሰኘዉ ተቋም በታችኛዉ ኦሞ ወንዝ አካባቢ የሚኖሩት ሰዎች ከመሬታቸዉ እንደተፈናቀሉ  እንድሁም ሌሎች ሰባዊ መብት ጥሰቶች እንደተፈፀመባቸዉ በመዝገብ ተይዘዋል ሲሉ የተቋሙ በጀርምን አስተባባሪ የሆኑት ልንዳ ፖፔ ለዶቼ ቬሌ ተናግረዋል። ግድቡ ተጠናቆ ስራ ላይ ቢዉሊም በነዋርዎቹ ፍቃድ ዉጭ ስለሆነ አሁንም ትችታችንን አላቆምነም ይላሉ።

«እንግዲህ ቀድም ብሎ ከአከባቢዉ ነዋርዎች ፍቃድ ስላልተሰጠ  አሁንም ችግሩ ቀጥለዋል። አሁንም የሰባዊ መብት ጥሰት ቀጥሎዋል። በዚህ ሁኔታም ደስተኛ አይደለንም። በመንግስት ላይ ጫና ማድረጋችንን እንዴ ስኬት ነዉ የምናየዉ። ረጅ አገሮችም ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ስለ ሰብአዊ  መብት ጥሰት እንደተነጋገሩ ነግረዉናል። ስለዚህ ዘመቻችን ትኩረት ሳያገኝ አለቀረም። ይሁን እንጅ የሰዎችን ፍቃድ እስካለገኙና የሰባዊ መብት ጥሰት በመቀጠሉ እኛንም አሳስቦናል፣ ጉዳዩንም ተከታትለን እንቆጣጠራልን።»

የግልገል ግቤ ግንባታ በ1998 መጨረሻ እንደተጀመረና ከ1,5 ቢሊዮን ዩሮ ወጭ እንደተደረገ አቶ ምስክር ተናግረዋል።

መርጋ ዮናስ

አዜብ ታደሰ 
 

Audios and videos on the topic