ግሪክና የስደተኞች ቀዉስ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 26.01.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

ግሪክና የስደተኞች ቀዉስ

ግሪክ የስደተኞች ጉዳይን በተመለከተ በምታራምደዉ ፖለቲካ ከአዉሮጳ ኅብረት አባል ሃገራት የሚሰነዘርባት ከፍተኛ ወቀሳና ትችት ተጠናክሮ ቀጥሎአል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:27
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
03:27 ደቂቃ

ግሪክና የስደተኞች ቀዉስ


የኦስትርያ የሀገር አስተዳደር ሚኒስትር ዮኃና ሚክል ላይትነር፣ ስደተኞች የመጀመሪያ መዳረሻ ያደረጉዋት የአውሮጳ ኅብረት አባል ግሪክ መንግሥት ጥብቅ የድንበር ቁጥጥር ካልጀመረ፣ የግሪክ የሸንገን አባልነት በጊዝያዊነት እንዲሰረዝ መፈለጋቸዉን ገልፀዋል። የጀርመን የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፍራንክ ቫልተር ሽታይን ማየር የኦስትርያ የሀገር አስተዳደር ሚኒስትር ያቀረቡትን ይህን ሀሳብ ወድያዉ ነዉ ዉድቅ ያደረጉት። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግሪክ በአዉሮጳ ኅብረት ርዳታ፤ አንድ የስደተኞች መቀበያና መመዝገብያ ማዕከል አቋቁማለች። በርግጥ ስደተኞችን የመቀበሉና የመመዝገቡ ሥራ ተሳክቶላት ይሆን?

Johanna Mikl-Leitner Österreich Gespräch Presse

የኦስትርያ የሀገር አስተዳደር ሚኒስትር ዮኃና ሚክል ላይትነር


በርካታ የአዉሮጳ ኅብረት አባል ሃገራት በተለይ ኦስትርያ፤ ግሪክ ከቱርክ ጋር የሚያዋስናትን ድንበር በበቂ አትቆጣጠርም ሲሉ ወቀሳ ያሰማሉ። አብዛኞቹ ስደተኞች ከሶርያ፤ ከአፍጋኒስታንና ከኢራቅ፣ ሜዲተራንያን ባህርን አቋርጠዉ ወደ አዉሮጳ ኅብረት ሃገራት ይገባሉ። እንደ ርዳታ ድርጅቶች ገለፃ በግሪክ ለስደተኞች ያለዉ ሁኔታ አሁንም አልተሻሻለም። የኦስትርያ የሃገር አስተዳደር ሚንስትር ዮሃና ሚክል ላይትነር እንደተናገሩት ግሪክን ለጊዜዉ ከሸንጌን አባልነት መሰረዝ ይሻል።

«እንደኔ እምነት የአዉሮጳ ኅብረት ሃገራት የዉጭ ድንበርን ማለትም የግሪክ ቱርክ ድንበርን መቆጣጠር ካልቻለ፤ የሸንጌን አባል ሃገራት የዉጭ ድንበር ወደ መሃል አውሮጳ ይሳባል። ስለዚህ ግሪክ በፍጥነት ያላትን አቅም ሁሉ እንድታጠናክር እና ለዚህም ርዳታና ድጋፍ እንድትቀበል ትጠየቃለች።»

ወደ ሌሎች አዉሮጳ ሃገራት ማለፍ የሚፈልጉ ከኢራቅ፤ ከሰሜን አፍሪቃ የመጡ በርካታ ስደተኞች ግሪክ ዉስጥ ይገኛሉ። የግሪክ መንግሥት እነዚህ ስደተኞች የተገን ጥያቄ እንዲያቀርቡ እድል ቢሰጥም፤ አብዛኞቹ ስደተኞች ራሳቸዉን ማስመዝገብ አይፈልጉም። ስደተኛው ፓኪስታናዊዉ ሶሃድ እንደሚለው፣ በግሪክ ምንም ዓይነት እድል የለም።

Demonstration Griechenland Türkei Grenze

በቱርክ ግሪክ ድንበርላይ ሰላማዊ ሰልፍ


« እኛ ላይ ያላቸዉ ደንብ በጣም ጠንካራ ነዉ። ወደ ሌላ ሃገር እንድንሄድ አይለቁንም። እዚህ ሥራ ከጀመርክ የሚሰጡህ ገንዘብ ደግሞ በቂ አይደለም። »
አቴንስ ዉስጥ የሚገኝ አንድ ስታድዮም ስር ከፓኪስታን እና ከሌሎች ሃገራት ለመጡ ስደተኛ ወንዶች መኖርያ አዳራሽ አለ። መኖርያ አዳራሹ የመተኛ አልጋ በቂ መፀዳጃ ቦታ ስለሌለዉ፤ እንደ መኖርያ ቦታ ጥሩ አይደለም። አቴንስ ዉስጥ ፕራክሲስ የተሰኘዉ የርዳታ ድርጅት አንድ አዲስ ባቀረበዉ ፕሮዤ በመቶዎች የሚቆጠሩ ስደተኞችን ርዳታ መስጠት ጀምሮአል። ድርጅቱ በሚቀጥሉት ሳምንታት ለ 20 ሺህ የሚበቃ ቦታን እንደሚያዘጋጅም ገልፆአል።
የአዉሮጳ ሕብረት ሃገራት አንድ ዉሳኔ ላይ እንዲደርሱ ዳግም ያስጠነቀቁት የኅብረቱ ኮሚሽነር ዲሚትሪስ አቫራሞፑሉስ በበኩላቸዉ ከኅብረቱ አባል ሃገራት ጀርመን አሁንም አብዛኛዉን ስደተኛ ከለላ እየሰጠች ያለች ብቸኛ ሃገር መሆንዋን ተናግረዋል። ኦስትርያ የድንበር ጉዳይን በተመለከተ የራስዋ የሆነ ሕግ ካፀደቀች በኋላ ቢያንስ እስከ ሚቀጥለዉ የበጋ ወራት ላይ ስደተኞችን መቀበል እንደምታቆም ነዉ የተናገሩት።
« ሁኔታዉን የማሳለፉ ጉዳይ የአባል ሃገራቱ ነዉ። በሌላ በኩል በሸንጌን አባል ሃገራት መካከል የነፃ ዝዉዉርን ለማረጋገጥ፤ የዉጭ ድንበሮቻችንን ለመቆጣጠር የተሻለ እቅድና አሰራር እንዲኖረን ማስፈለጉ ግልፅ ነዉ።»

Flüchtlinge Grenze Mazedonien Serbien Balkan Route Winter Kälte

ስደተኞች በባልካን ሃገራት፤ መቂዶንያ፤ ሰርቢያ


አሁንም በሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች ወደ ግሪኳ ደሴት ይተማሉ። በያዝነዉ የአዉሮጳዉያኑ ዓመት 2016 የመጀመርያ ወር ብቻ ግሪክ የደረሱት ስደተኞች ቁጥር ባለፈዉ ዓመት የመጀመርያ ወር ከደረሱት በሦስት እጥፍ ይበልጣል። በዚህም በአዲስ ወደ ግሪክ የሚገቡ ስደተኞችን « Hotspots » በተሰኘዉ ማዕከል ከተመዘገቡ በኋላ የተሰደዱበትን ምክንያት ማለት በኤኮኖሚ አልያም በጦርነት ሰበብ መሰደዳቸዉ ከተጣራ በኋላ ወደ ሌላ ቦታ ማከፋፈል ይቻላል። ይህ የስደተኞች መመዝገብያ ማዕከል ጥሩና ከፍተኛ ጅማሮ መሆኑን በአቴንስ የአዉሮጳ ኅብረት ኮሚሽነር ቤሮ ዋና ተጠሪ ፓኖስ ካርቩኒስ ተናግረዋል።

«ግሪክ ስደተኞችን ምዝገባና ቁጥጥር ላይ እጅግ መዘግየትዋን አምናለች። እንድያም ሆኖ ከአዉሮጳ ኅብረት ኮሚሽንና በሌሎች ድርጅቶች በመታገዝ « Hotspots » የተሰኘ ማዕከል በሚቀጥለዉ ሳምንታት ሙሉ ስራዉን ይጀምራል ብዩ አምናለሁ።»

ዎልፍጋንግ ላንድ ሜሰር / አዜብ ታደሰ


አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic