ግልፅ ደብዳቤ ለጠ/ሚ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ | ኢትዮጵያ | DW | 16.10.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ግልፅ ደብዳቤ ለጠ/ሚ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ

ደብዳቤው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የተላከው አዲሱ ካቢኔ በዚህ የሃገር ጉዳይ ላይ እንዲወያይና ጠቅላይ ሚኒስትሩም በጉዳዩ ላይ ከህዝቡ ጋር እንዲመክሩበት ለመሳሳበብ መሆኑን የማህበሩ ስራ አስኪያጅ አቶ ፋንታሁን ብርሃኑ ለዶቼቬለ ተናግረዋል ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:19
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
03:19 ደቂቃ

ግልፅ ደብዳቤ

ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉትን ልዩ ልዩ ችግሮች ለመፍታትና በሃገሪቱም እርቀ ሰላም ለማውረድ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ወገኖች ጋር ውይይት እንዲካሄድ ጥሪ ቀረበ ። የመግባባት አንድነትና ሰለም ማህበር የተሰኘው ሃገር በቀል መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ጉዳዩ ቅድሚያ ትኩረት እንዲሰጠው ለኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ለአቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ በዚህ ሳምንት በላከው ግልፅ ደብዳቤ ጠይቋል ። ደብዳቤው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የተላከው አዲሱ ካቢኔ በዚህ የሃገር ጉዳይ ላይ እንዲወያይና ጠቅላይ ሚኒስትሩም በጉዳዩ ላይ ከህዝቡ ጋር እንዲመክሩበት ለመሳሳበብ መሆኑን የማህበሩ ስራ አስኪያጅ አቶ ፋንታሁን ብርሃኑ ለዶቼቬለ ተናግረዋል ።አቶ ፋንታሁን እንዳሉት የማህበሩ ደብዳቤ እስካሁን መልስ አላገኘም።ስለ ደብዳቤው ዶቼቬለ የጠየቀው የመንግሥት ኪሚኒኬሽን ሚኒስቴር ፣ደብዳቤው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ፅህፈት ቤት አልደረሰም ብሏል ። የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ዝርዝሩን ልኮልናል ።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ኂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic