″ጋዜጠኝነት አንደበት ነው″ - መላኩ ብርሃኑ | ባህል | DW | 16.06.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ባህል

"ጋዜጠኝነት አንደበት ነው" - መላኩ ብርሃኑ

በአዲስ አበባ የቴሌቢዥን ፖሊስ ፕሮግራም ብዙዎች ያስታውሱታል። አሁን ደግሞ በአርቲስ ቲቢ በአብይ ጉዳይ የቴሌቢዥን ፕሮግራም አዘጋጅ ነው፤ ጋዜጠኛ መላኩ ብርሃኑ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 10:16

ጋዜጠኛ መላኩ ብርሃኑን

መላኩ በአርቲስት ቲቪ ዓብይ ጉዳይ በሚል እንግዶችን አሳታፊ የውይይት ፕሮግራም በማዘጋጀት ይታወቃል። ከዚህ ቀደም በአዲስ ቲቪ የፖሊስ ፕሮግራም አዘጋጅ ነበር። ለ18 ዓመታት በጋዜጠኝነት ሙያ አገልግሏል። በተለያዩ የመገናኛ ብዙኃኖች ውስጥ በሙያውና በኃላፊነት ቦታዎች ላይ ሰርቷል። ጋዜጠኝነት በአጋጣሚ የገባበት ሙያ እንዳልሆነ መላኩ ይናገራል። ሲመኘው የነበረው ሙያ ነበር። የሥነ-ጽሁፍ ፍላጎቱ ወደ ሙያው አስገብቶኛልም ይላል። ጋዜጠኛ ለመሆን የውስጥ ፍላጎት ያስፈልጋል የሚለው መላኩ ብዙ እውነቶችን በጽሁፍ የመግለጽ ችሎታም እንደሆነ ይናገራል። መላኩ የሁለት ልጆች አባትም ነው። የአንድ ሴትና የአንድ ወንድ ልጅ። ተግባቢ መሆኑን እራሱ ስለራሱ ባህሪ ይመሰክራል። በርግጥም ስለራስ መመስከር ከባድ ቢሆንም ይላል መላኩ። ሙሉው ዝግጅት ማገናኛው ላይ ይገኛል

ነጃት ኢብራሂም

አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic