ጋዜጠኛ ጌታቸዉ ሽፈራዉ ተፈረደበት | ኢትዮጵያ | DW | 26.05.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ጋዜጠኛ ጌታቸዉ ሽፈራዉ ተፈረደበት

የሰማያዊ ፓርቲ ስልሳን የሆነዉ የነገረ ኢትዮጵያ ዋና አርታኢ ጋዜጠኛ ጌታቸዉ ሽፈራዉ የአንድ ዓመት ከስድስት ወር እስራት ተፈረደበት። ጠበቃ አመሃ መኮንን ዛሬ ለዶይቼ ቬለ በሰጡት መግለጫ ጋዜጠኛ ጌታቸዉ ሽፈራዉ እስር ቤት አንድ ዓመት ከአምስት ወር በማሳለፉ በአመክኖ ይፈታል ብለን እናስባለን ሲሉ አስታውቀዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:07

የጋዜጠኛ ጌታቸዉ ሽፈራዉ ብይን

 ክሱን የመብት ተሟጋቾች ፕረስ ነፃነት ላይ የተሰነዘረ ጥቃት ብለዉታል። እንደ አዣንስ ፍራንስ ፕረስ ዘገባ ከሆነም፤ ካለፈዉ ዓመት ታኅሳስ ወር ጀምሮ በእስር ላይ የሚገኘዉ ጋዜጠኛ ጌታቸዉ፤ ከተያዘበት አንስቶ ጊዜዉ ሲሰላ በቅርቡ ሊፈታ ይችላል። ዛሬ አዲስ አበባ ላይ በዋለ ሌላ ችሎት በኢሬቻ በዓል ላይ ለተፈጠረዉ ትርምስ ምክንያት ናቸዉ የተባሉ ሁለት ሰዎች በአሸባሪነት ክስ እንደተመሰረተባቸዉ ታዉቋል። ይህን ክስ አስመልክቶ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ሙላቱ ገመቹ፤ ክሱ ለኛ አዲስ ነዉ የምናጠናዉ ይሆናል ሲሉ ተናግረዋል። ሙሉዉን ዝርዝር ዘገባ የድምፅ ማድመጫ ማዕቀፉን በመቻን ያድምጡ።

አዜብ ታደሰ

አርያም ተክሌ  
 

Audios and videos on the topic