ጋዜጠኛ ኤልያስ እና ፖለቲከኛ ዳንኤል በዋስ እንዲለቀቁ ተፈረደ  | ኢትዮጵያ | DW | 17.07.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ጋዜጠኛ ኤልያስ እና ፖለቲከኛ ዳንኤል በዋስ እንዲለቀቁ ተፈረደ 

የኢትዮጵያ ፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ እና ፖለቲከኛ ዳንኤል ሺበሺ በዋስ እንዲለቀቁ ፈረደ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:19

የአቃቤ ሕግ አንድ ምሥክር በዝግ ችሎት መስክረዋል፤

ዛሬ ያስቻለው የኢትዮጵያ ፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ እና ፖለቲከኛ ዳንኤል ሺበሺ በዋስ እንዲለቀቁ ፈረደ። ችሎቱ የስር ፍርድ ቤት፣ የፍርድ ሂደቱ በዝግ እንዲታይ የሰጠውን ብይን በተመለከተ ለምስክሩ ጥበቃ ሲባል በማለት የስር ፍርድ ቤት ውሳኔን አጽድቋል። በዚሁ መሠረትየአቃቤ ህግ ምስክር የሆኑት አንድ የደህንነት አባል  ዛሬ በዝግ ችሎት መመስከራቸውን የአዲስ አበባው ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዘግቧል.
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ኂሩት መለሰ
 

Audios and videos on the topic