ጋዘጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ተፈታ | ኢትዮጵያ | DW | 29.08.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ጋዘጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ተፈታ

መቀመጫውን ኒውዮርክ ያደረገው የጋዜጠኞች መብት ተሟጋቹ ድርጅት CPJ በጋዜጠኛ ተመስገን መለቀቅ መደሰቱን አስታውቆ ሌሎች የታሰሩ ጋዜጠኞችም እንዲፈቱ ጥሬ አቅርቧል ።የኢትዮጵያ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ በፍትሕ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ በተመስገን ደሳለኝ ላይ መሥርቶት የነበረዉን ክስ መቋሩጡን የመንግሥት ባለሥልጣናት አስታወቁ።ጋዜጠኛ ተመስገን በቅርቡ አመፅና ሁከት የሚቀሰቅስ ዘገባ አዘጋጅቷል የሚል ክስ ተመስርቶበት ባለፈዉ ሐሙስ ታስሮ ነበር።ትናንት ተለቋል።የተመሰረቱበት 3 ክሶችም መቋረጣቸው ተነግሯል ተመስገን የተለቀቀበትን ምክንያት በትክክል አያዉቀዉም።የኢትዮጵያ መንግሥት ቃል አቀባይ አቶ ሽመልስ ከማል እንዳስታወቁት ግን አቃቤ በተመስገን ላይ የመሠረተዉን ክስ የሠረዘዉ ወይም ያቋረጠዉ ሐገሪቱ መሪዋን በሞት አጥታ ሕዝቡ ሐዘን ላይ በመሆኑ ነዉ።ተመስገን በዋና አዘጋጅነት የሚመራዉ የፍትሕ ጋዜጣ የተወሰኑ እትሞች እንዳይሰራጩ፥ ያልታተመዉ ደግሞ እንዳይታተም ታግዶም ነበር።የጋዜጣዉ ቅጂ አለመታተሙና የተመስገንን መታሰር የተለያዩ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅቶችና ተቋማት አዉግዘዉት ነበር።መቀመጫውን ኒውዮርክ ያደረገው የጋዜጠኞች መብት ተሟጋቹ ድርጅት CPJ በጋዜጠኛ ተመስገን መለቀቅ መደሰቱን አስታውቆ ሌሎች የታሰሩ ጋዜጠኞችም እንዲፈቱ ጥሬ አቅርቧል ።

ነጋሽ መሐመድ

ሒሩት መለሰ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች