1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጋቦን አዲስትዋን ጠቅላይ ሚኒስትር ሾመች

ዓርብ፣ ሐምሌ 10 2012

የቀድሞ ጋቦን መከላከያ ሚኒስትር ሮስ ክርስትያን ራፓንዳ የጋቦን ጠ/ሚ ሆነዉ ተሾሙ። ራፓንዳ በጋቦን ጠ/ሚ ሆነዉ የተሾሙ ሴት ባለስልጣን ናቸዉ። በጎርጎረሳዉያኑ 2009 ዓ.ም ከአባታቸዉ መንበር ስልጣኑን የተረከቡት ፕሬዚዳንት አሊ ቦንጎ፤  የ 56 ዓመትዋ አዲስዋ የጋቦን ጠ/ሚ ሮስ ክርስትያን ራፓንዳ ስድስተና ጠቅላይ ሚኒስትር መሆናቸዉ ነዉ።

https://p.dw.com/p/3fVtm
Gabon | neue Premierministerin Rose Christiane Ossouka Raponda
ምስል Getty Images/AFP/J. Tatou

 

የቀድሞ ጋቦን መከላከያ ሚኒስትር ሮስ ክርስትያን ራፓንዳ የጋቦን ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነዉ ተሾሙ። ራፓንዳ በጋቦን ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነዉ የተሾሙ ሴት ባለስልጣን ናቸዉ። በጎርጎረሳዉያኑ 2009 ዓም ከአባታቸዉ መንበር ስልጣኑን የተረከቡት ፕሬዚዳንት አሊ ቦንጎ፤  የ 56 ዓመትዋ አዲስዋ የጋቦን ጠቅላይ ሚኒስትር ሮስ ክርስትያን ራፓንዳ ስድስተና ጠቅላይ ሚኒስትር መሆናቸዉ ነዉ። ራፓንዳ  በጎርጎረሳዉያኑ 2014 የጋቦን መዲና ሊቨርፑል ከንቲባም ሆነዉ ተሾመዉ ነበር። ራፓንዳ በጋቦን ታሪክ ከጎርረሳዉያኑ 1956 ወዲህ የተመረጡ ከፍተኛ የሴት ባለስልጣን ናቸዉ። ከጎርጎረሳዉያን 2019 ዓም ጀምሮ የጋቦን መከላከያ ሚኒስትር ሆነዉ ሲያገለግሉ  ነበር። አዲስዋ ጠ/ሚ በአዲሱ ስልጣናቸዉ ጋቦን ያለባት የኮሮና ስርጭት ጉዳይ ተግዳሮት እንደሚሆንባቸዉ ተገምቶአል። ማዕከላዊ አፍሪቃዊትዋ ሃገር ጋቦን በአንድ ቀን እስከ 6000 ሰዎች በኮሮና የተያዙ ሰዎች ስለመኖራቸዉ በምርመራ እየተረጋገጠ ነዉ።

 

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ