ጊቤ 3 የኃይል ማመንጫ ተመረቀ | ኢትዮጵያ | DW | 18.12.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ጊቤ 3 የኃይል ማመንጫ ተመረቀ

እሁድ ታኅሣሥ 8 ቀን 2009 ዓ.ም. የምረቃ ስነ-ሥርዓት የተከናወነለት የግልገል ጊቤ ሦስት የኃይል ማመንጫ ግድብ በከፊል ሥራ መጀመሩ ተገለጠ።

ኢትዮጵያ በ1.5 ቢሊዮን ዩሮ (1.57 ቢሊዮን ዶላር) በኦሞ ወንዝ ላይ የተገነባውን የኃይል ማመንጫ አስመረቀች። 1,870 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም አለው የተባለው የጊቤ ሦስት በጣልያኑ ሳሊኒ ኩባንያ የተገነባ ሲሆን፤ የአገሪቱን የማምረቻ ዘርፍ እና ለጎረቤት አገራት የምትሸጠውን የኤሌክትሪክ ኃይል ያሳድጋል ተብሎ ተስፋ እንደተጣለበት ሮይተርስ የዜና ምንጭ ዘግቧል። በገንዘብ እጥረት የተጓተተውን የኃይል ማመንጫ ግንባታ የቻይናው ኢምፖርት ኤክስፖርት ባንክ 60 በመቶ ወጪ በብድር መሸፈኑን የዜና ምንጩ አክሏል።

ኢትዮጵያ በደቡባዊ የሀገሪቱ ክፍል በሚገኘው የኦሞ ወንዝ ላይ 2,000 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ያለው አራተኛ የኃይል ማመንጫ ለመገንባት ማቀዷን ባለፈው መጋቢት አስታውቃለች። ኢትዮጵያ ወደ ኬንያ፤ ሱዳን እና ጅቡቲ የኤሌክትሪክ ኃይል የምትልክ ሲሆን፤ ከታንዛኒያ፣ርዋንዳ፣ ደቡብ ሱዳን እና የመን ጋር ደግሞ ውል ገብታለች።

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ/እሸቴ በቀለ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

Audios and videos on the topic