ገጣሚ በላይ በቀለ ወያ | ባህል | DW | 14.04.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ባህል

ገጣሚ በላይ በቀለ ወያ

ከባሻገር ባሻገር፤ እንቅልፍ እና ሴት፤ እየሄዱ መጠበቅ፤ እንዲሁም ከሴተኛ አዳሪ የተኮረጀ ሳቅ የተሰኙ የግጥም እና ወግ መድብሎችን በተከታታይ ባለፉት ዓመታት አሳትሟል። አፍቄሜሌፅ በሚል ርዕስም የተዘጀ የግጥም ሲዲ ለስነጽሑፍ ቤተሰቦች አቅርቧል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 10:11

«የግጥም ታዳሚያን መበራከታቸውን ዕድል ይለዋል»

ስለትምህርት ስናወራ እየተማረ ሞተ ብባል ይሻለኛል እና በዚህ ምክንያት ዛሬም ተማሪነኝ ነው ያለኝ። ስነግጥምን የሚገልፅበት ቃል እንደሌለው የሚናገረው ገጣሚ በላይ በቀለ ወያ ለሀገሩ ለኢትዮጵያ ያለው ፍቅር ደግሞ ከምንም እንደሚበልጥበት አጫውቶኛል። 

ግጥሞችን መጻፍ ከጀመረ ስድስት ሰባት ዓመታት እንደሆኑት የሚናገረው በላይ በቀለ ወያ፤ ሙሉ ጊዜውን ለኪነጥበብ እና ስነጽሑፍ ሰጥቷል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ በወር አንድ ቀን ማክሰኞ የግጥም ምሽት ከባልደረባው ጋር በመሆን ያዘጋጃል። ካለፉት ጥቂት ዓመታት ወዲህ የግጥም ምሽቶች እየተበራከቱ ታዳሚዉም ቁጥሩ እየጨመረ መሄዱንም አስተውሏል። ጎህ በተሰኘው የግጥም ምሽቱ እስከ አንድ ሺህ ሰዎች ይታደማሉ። የእሱን እና የባልደረቦቹን የጥበብ ሥራዎች በአካል ለማድመጥም ወር በገባ በሁለተኛው ሳምንት ማክሰኞ ዋቢ ሸበሌ ሆቴል ብቅ ያለ መንፈሱን አርክቶ እንደሚመለስ ነው ከቆይታችን የተገነዘብኩት።

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic