ገና እና ላሊበላ | ኢትዮጵያ | DW | 07.01.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ገና እና ላሊበላ

ከኢትዮጵያ እውቅ የአገር ጎብኚዎች መዳረሻ አንዱ የሆነው የላሊበላ ውቅር አብያተ-ክርስቲያናት ላስታ ቡግና ወረዳ፤ ሮሃ ከተባለች ቦታ ይገኛል። ከድንጋይ ተፈልፍለው የታነጹ አብያተ-ክርስቲያናት የያዘው አካባቢ የተሰየመው በንጉስ ላሊበላ ስም ነው።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 06:08
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
06:08 ደቂቃ

ገና እና ላሊበላ

ቅዱስ ላሊበላ ሲወለድ በንቦች ተከቦ እንደነበረና እናቱም በክስተቱ በጣም እንደተገረመች ይነገራል። «ከእናቱ ከወተት በፊት ማር አቀመሱት ምን አይነት ተአምር ነው» በማለት ስሙን ላልይበላ አለችው ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ይተርካሉ። ላል በአገውኛ ማር አለያም ንብ ማለት ነው። ላልይበላ ማለት ማር ይበላል ማለት ነው። የገና በዓል 11 ውቅር-አብያተ ክርስቲያናት በሚገኙበት የላሊበላ አካባቢ በድምቀት ይከበራል። አገር ጎብኚዎች እና ምዕምናን የሚያዘወትሩት የገና በዓል አከባበር ምን ይመስላል? አካባቢውስ ለአገር ጎብኚዎች ምን ያክል ምቹ ነው? ወደ ስቱዲዮ ከመግባቴ በፊት በኢትዮጵያ ባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር የህዝብ እና የውጭ ግንኙነት ክፍል ኃላፊ የሆኑትን አቶ ገዛኸን አባተን በስልክ አነጋግሪያቸዋለሁ።

እሸቴ በቀለ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች