ጆ ባይደን በባልካን | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 20.05.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

ጆ ባይደን በባልካን

ጆ ባይደን ጉብኝታቸው ከተለያየ ወገን ይፋዊ ተቃውሞ እንደደረሰበትም ታውቓል። ምክትል ፕሬዚዳንቱ እግራቸው የሰርቢያ ዋና ከተማ የቤልግሬድን መሬት በረገጠ ቅፅበት አንድ የሰርቢያ ፅንፈኛ ብሔረተኛ በቴሌቪዥን ጆ ባይደንን መሳደባቸው ተገልጿል።

ጆ ባይደን ከሰርቢያው ፕሬዚዳንት ጋር

ጆ ባይደን ከሰርቢያው ፕሬዚዳንት ጋር

የዩናይትድ ስቴትሱ ምክትል ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ለሶስት ቀናት የባልካን ሀገራት ጉብኝት ሰርቢያ ይገኛሉ። በጉብኝታቸውም፤ ሰርቢያ ነፃ ለሆነችው የቀድሞ ግዛቷ ኮሶቮ እውቅና እንድትሰጥ ዩናይትድ ስቴትስ አትጠብቅም ማለታቸውን አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘገበ። ለኮሶቮ ከሰርቢያ መገንጠል ዩናይትድ ስቴትስ ከፍተኛ ሚና እንደተጫወተች ሲታወቅ፤ ለአዲሲቷ ሀገር ኮሶቮም እውቅና በፍጥነት ነበር የሰጠችው። የጆ ባይደን የጉብኝት ዓላማ በባልካን አካባቢ መረጋጋት እንዲፈጠር መጣር እንደሆነም ተገልጿል።

ማንተጋፍቶት ስለሺ