ጆን ኬሪ በአዲስ አበባ | ኢትዮጵያ | DW | 02.05.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ጆን ኬሪ በአዲስ አበባ

ትናንት ማምሻዉን አዲስ አበባ የገቡት የአሜሪካን የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ ኢትዮጵያ ለሲቪክ ማኅበራትና ለጋዜጠኞች የተሻለ ነፃነት እንድትሰጥ ጠየቁ። ባለፈዉ ሳምንት ማለቂያ የታሠሩት የድረገፅ ጸሀፍትና ጋዜጠኞች ጉዳይም እንዳሳሰባቸዉ ገለጹ።

ባለፈዉ ሳምንት ማለቂያ የታሠሩት የድረገፅ ጸሀፍትና ጋዜጠኞች ጉዳይም እንዳሳሰባቸዉ ገለጹ። ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ጋ ከተነጋገሩ በኋላ ኬሪ፤ ኢትዮጵያ ዉስጥም ሆነ የትም ቦታ የሚታሠሩ ጋዜጠኞች ጉዳይ እንደሚያሳስባቸዉ መግለፃቸዉን ማመልከታቸዉን የፈረንሳይ የዜና ወኪል ከአዲስ አበባ ዘግቧል። ጋዜጠኞች በህትመት፤ በኢንርኔትም ሆነ በትኛዉም ዓይነት መገናኛ ብዙሃን የሚያከናዉኑት ኅብረተሰቡን እንደሚያጠናክር፤ እንደሚያነቃቃና ፤ለዴሞክራሲም መጠናከርና ድምፅ ሊሆን እንደሚችልም ገልጸዋል። የመብት ተሟጋቾች በዓለማችን እጅግ የተዘጋ የፕረስ ሁኔታ ያላት ሀገር ኢትዮጵያ ናት በማለት ይተቻሉ። ጆን ኬሪ በሰጡት መግለጫ የጸረ ሽብር ሕግን ሃሳብን በነፃነት የመግለጽ መብትን ለማገጃ ሊናዉል አይገባም ማለታቸዉን ዘገባዉ ጨምሮ ጠቅሷል።

የዩናይትድ ስቴትስ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪን የአፍሪቃ ጉብኝት በደቡብ ሱዳን የተካሄደዉ የዘር ፍጅት ሳያጠላበት እንዳልቀረ ተገልጿል። የፈረንሳይ የዜና ወኪል አዣንስ ፍራንስ ፕረስ ስፍራዉ እንደዘገበዉ ትናንት አመሻሹ ላይ አዲስ አበባ የገቡት ኬሪ ከኢትዮጵያ፣ ኬንያና ዩጋንዳ አቻዎቻቸዉ ጋ ባካሄዱት ዉይይት ግጭቱ ከፍተኛዉን ስፍራ ይዟል። በደቡብ ሱዳን በፕሬዝደንት ሳል ቫኪርና በቀድሞ ምክትላቸዉ ሪክ ማቻር ታማኞች መካከል የሚካሄደዉን ዉጊያ ለማስቆምም የአካባቢዉ ሃገራት ወታደሮች በሚልኩበት ሁኔታ ላይም ተነጋግረዋል። ኬሪ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫም ግድያ እንዲቆም ሁሉም ይስማማል ብለዉ እንደሚያስቡ እና ሰብዓዊ ርዳታም መዳረስ እንደሚኖርበት አመልክተዋል። የአሜሪካን የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር በዛሬዉ ዕለትም ከአፍሪቃ ኅብረት መሪዎች ጋ ደቡብ ሱዳን ብቻ ሳይሆን ማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፑብሊክ ዉስጥም ያለዉን ግጭት በተመለከተ እንደሚነጋገሩ ተገልጿል። ጆን ኬሪ ሃገራቸዉ አፍሪቃ ግጭቶችን ለማስወገድ የምታደርገዉን ጥረት እንደምትደግፍም አስታዉቀዋል።

በማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፑብሊክ ለመግለጽ የሚያዳግተዉ አመፅ እንዲሁም ደቡብ ሱዳን ዉስጥ ሆን ብሎ ሲቪሎችን የመግደል ርምጃ አስቸኳይ የጋራ ትብብር እንደሚጠይቅም ገልጸዋል። ኬሪ ቀደም ሲል ዛሬ ጠዋት የምሥራቅ አፍሪቃ ሃገራት በአፋጣኝ ሰለም አስከባሪ ኃይሎችን ወደ ደቡብ ሱዳን እንዲልኩ ተማፅነዋል ። 6 ወራት ለሚጠጋ ጊዜ የዘለቀውን ንየደቡብ ሱዳን ግጭት ለማስቆም ወደ ሃገሪቱ የሰላም አስከባሪዎች መላካቸው እጅግ አንገብጋቢ መሆኑን ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ ላነጋገሯቸው የኢትዮጵያ የኬንያ ና የዩጋንዳ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አስታውቀዋል ። ኬሪ ያነጋገሯቸው እነዚሁ ዲፕሎማቶች በደቡብ ሱዳን የሚካሄደው ግድያ እንዲቆም ጠንካራ እርምጃ መውሰድ እንደሚገባ መስማማታቸውን አስታውቀዋል።

የኬሪን ጋዜጣዊ መግለጫ የተከታተለው የአዲስ አበባው ወኪላችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ዝርዝሩን ልኮልናል ።

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ሂሩት መለሰ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic