ጅቡቲ ደርሶ መልስ-ጠቅላይ ምኒስትር አብይ አሕመድ  | ኢትዮጵያ | DW | 30.04.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ጅቡቲ ደርሶ መልስ-ጠቅላይ ምኒስትር አብይ አሕመድ 

ጠቅላይ ምኒስትር አብይ አሕመድ ወደ ጅቡቲ አቅንተው ከፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦማር ጉሌሕ እና ከፍተኛ የመንግሥት ሹማምንት ጋር ውይይት አድርገዋል። በጅቡቲ ቆይታቸው ወደቦች ጭምር ጎብኝተዋል። በአገሪቱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተውም ንግግር አድርገዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:34

የጠቅላይ ምኒስትር አብይ የጅቡቲ ጉብኝት

ከጅጅጋ እስከ መቀሌ ከአምቦ እስከ ባሕር ዳር ተከታታይ ጉዞዎች እና የምክክር መድረኮች ላይ የከረሙት ጠቅላይ ምኒስትር አብይ አሕመድ የመጀመሪያ የውጭ አገር ጉብኝታቸውን አድርገዋል። ጠቅላይ ምኒስትሩ ወደ ጅቡቲ አቅንተው ከፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦማር ጉሌሕ እና ከፍተኛ የመንግሥት ሹማምንት ጋር ውይይት አድርገዋል። በጅቡቲ ቆይታቸው ወደቦች ጭምር ጎብኝተዋል። በአገሪቱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተውም ንግግር አድርገዋል። የአዲስ አበባው ወኪላችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ የሆኑትን አቶ መለስ አለምን በማነጋገር የሚከተለውን ዘገባ አድርሶናል። 
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
እሸቴ በቀለ
አርያም ተክሌ 

Audios and videos on the topic