ጄኮብ ዙማ እና የተቀሰቀሰባቸው የሙስና ክስ | ኢትዮጵያ | DW | 13.01.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ጄኮብ ዙማ እና የተቀሰቀሰባቸው የሙስና ክስ

የሀገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት እንዳስረዳው ከዚህ ቀደም በዙማ ላይ የተመሰረተው የሙስና ክስ እንዲሰረዝ በከፍተኛው ፍርድ ቤት የተላለፈው ውሳኔ ስህተትና መሰረታዊ ህጋዊ ደረጃዎችንም ያልጠበቀ ነበር ።

default

ጄኮብ ዙማ

በደቡብ አፍሪቃ የፊታችን ሚያዚያ በሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የአፍሪቃ ብሄራዊ ምክር ቤቱ መሪ ጄኮብ ዙማ በቀላሉ ድል እንደሚጎናፀፉ እስከትናንት ድረስ አንዳችም አጠራጣሪ ነገር አልነበረም ። ሆኖም ዙማ ያለ መሰናክል ማሸነፍ መቻላቸው እንዲያውም ከነአካቴው ለፕሬዝዳንትነት ለመወዳደር መብቃታቸው ከትናንት አንስቶ ማነጋገር ጀምሯል ።