ጄነራል ሰዓረ መኮንን መገደላቸውን ሕወሓት አረጋገጠ | ኢትዮጵያ | DW | 23.06.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ጄነራል ሰዓረ መኮንን መገደላቸውን ሕወሓት አረጋገጠ

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄነራል ሰዓረ መኮንን እና ሜጀር ጄነራል ገዛኢ አበራ መሞታቸውን የድምፀ ወያኔ ቴሌቪዥን ጣቢያ አስታወቀ። የጄነራል ሰዓረ እና የሜጀር ጄነራል ገዛኢን ሞት ተከትሎ የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች ዛሬ ንጋት ለስብሰባ ተቀምጠው እንደነበር የዶይቼ ቬለ የመቀሌ ወኪል ሚሊዮን ኃይለስላሴ ከስፍራው ዘግቧል

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄነራል ሰዓረ መኮንን መሞታቸውን የድምፀ ወያኔ ቴሌቪዥን ጣቢያ አስታወቀ።

ጣቢያው ሜጀር ጄነራል ገዛኢ አበራ መሞታቸውን ጨምሮ ገልጿል። የጄነራል ሰዓረ መኮንንን እና የሜጀር ጄነራል ገዛኢ አበራን ሞት ተከትሎ የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከፍተኛ አመራሮች ዛሬ ንጋት ለስብሰባ ተቀምጠው እንደነበር የዶይቼ ቬለ የመቀሌ ወኪል ሚሊዮን ኃይለስላሴ ከስፍራው ዘግቧል።

ስብሰባውን ያካሄዱት የህወሓት ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ናቸው። ህወሓት በትግራይ ክልል ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ዛሬ ጠዋት ባሰራጨው መግለጫ በሁለቱ ከፍተኛ ወታደራዊ ሹማምንት ላይ "በቅጥረኞች ግድያ ተፈጽሞባቸዋል" ብሏል።

የህወሓት ሊቀመንበር እና የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ከጥቂት ቆይታ በኋላ መግለጫ ይሰጣሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው።

ተዛማጅ ዘገባዎች