ጃፓን ፤ የተፈጥሮው ኃያል ድቀት ካጋጠማት ፤ ከአሥራ-አንድ ቀናት ወዲህ፣ | ዓለም | DW | 22.03.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

ጃፓን ፤ የተፈጥሮው ኃያል ድቀት ካጋጠማት ፤ ከአሥራ-አንድ ቀናት ወዲህ፣

በሰሜን ምሥራቅ ጃፓን ፤ በኀያልነቱ ፣ እስካሁን ወደር ያልተገኘለት በሪኽተር መለኪያ 9,0 የደረሰ ብርቱ የምድር ነውጥና እጅግ ኃይለኛ የውቅያኖስ ማዕበል(ሱናሚ)ባለፈው ዓርብ መጋቢት 2, በጃፓን የቀን ስሌት ቅዳሜ፣

default

መጋቢት 3 ,2003 ከባድ ጥፋት ካደረሰ ወዲህ፣ እስካሁን በይፋው መግለጫ መሠረት ፤ ህይወታቸውን ያጡት 9,000 ሲሆኑ ከ 12,000 በላይ ደግሞ ደብዛቸው እንደጠፋ ነው። በፉኩሺማ የአቶም ኃይል ማመንጫ አውታሮች ለደረሰባቸው ሳንክ መላውን እንዴት ማግኘት አቃተ?እንዴት ብርቱ ጥፋት ሊደርስ ቻለ? የሰሜን ምሥራቅ ጃፓን የወደፊት ዕጣ -ፈንታ ምን ይሆን!?

በሰሜን ምሥራቅ ጃፓን፣ ፉኩሺማ ላይ ከሚገኙት የአቶም ኃይል ማመንጫ ጋኖች፣ የተደቀነው ሥጋት እስካሁን ሊወገድ አልቻለም። ከአቶም ኃይል ማመንCA አውታሮቹ፤ ጭስ እየወጣና ደመና እየመሰለ ከባቢ አየር ጋር በመቀላቀል ላይ ሲሆን፣ የዓለም አቀፉ የአቶም ኃይል ምንጭ ተቋም ባለሥልጣናት በቦታው በመገኘት፣ አደጋውን ለመግታት የሚደረገውን ጥረት ከመከታተል ባሻገር የአደገኛውን ጨረር መጠን ይለካሉ። ዋና ጽ/ቤቱ በኦስትሩሪያ ፣ ቪየና የሚገኘው የዓለም አቀፉ የአቶም ኃይል ምንጭ ተቋም ባልደረባ ግራሃም አንድርው --

«የመሻሻል ሁኔታ መኖሩን ብናይም፤ በፉኩሺማ ዲቺ ያለው አጠቃላይ ይዞታ አሁንም እጅግ የሚያሳስብ ነው። በአቶም ኃይል ማመንቻዎቹ ጋኖች፣ መጠኑን ያለፈ የመርዘኛ ጨረር ልቀት ማጋጠሙን በመለካት ደርሰንበታል።»

በአቶም ኃይል ማመንጫው ጋን ውስጥ፣ የኑክልየር ማገዶዎቹ ብርቱ ግለት ውሃው እየፈላ እንፋሎት እንዲፈጠር በማድረጉ፤ የአሳት አደጋ ተከላካዮች፤ በሚመጡት ቀናት፣ ውሃ በገፍ እየቀዱ በመቸለስ ለማቀዝቀዝ የሚያደርጉሹትን ጥረት መቀጠል ይኖርባቸዋል። አንድ የጃፓን የአቶም ኃይል አያያዝ ጉዳይ ባለሥልጣን ቃል አቀባይ፤ ተስፋ እንዳደረጉት ከሆነ፣ ለአቶም ኃይል ማመንጫ አውታሮቹ፣ ማቀዝቀዣ አውቶማቲክ መሣሪያ፣ የተቀጠለው ኤልክትሪክ ፣ እስከ ነገ ሊሠራ ይችላል። ማቀዝቀዣው መሣሪያ፣ በኤሌክትሪክ ኃይል እንደገና መሥራት ከጀመረ፣ በአንድ ቀን ውስጥ ተግባሩን በተሣካ ሁኔታ ሊያከናውን ይችላል የሚል እምነት አለ። ኤልክትሪኩ የተቋረጠው፣ በኃይለኛው የምድር ነውጥ እንደነበረ የሚታወስ ነው።

ከፉኩሺማ በስተሰሜን ምሥራቅ 100 ኪሎሜትር ራቅ ብሎ በሚገኘው ቦታ ፤ ዶ/ር ኬይኮ ያማዳ፣ በጭንቀት ላይ የሚገኙ በዛ ያሉ ሰዎችን ፣ የሰውነታቸውን አካላት ምን ያህል አደገኛ ጨረር እንዳገኛቸው በልዩ መሣሪያ ሲመረምሩ ነበረ የሰነበቱት።

«ሰዎቹ ተረብሸዋል። በተቻለ ፍጥነት አካባቢውን ለቀው መጓዝ ነው የሚፈልጉት። ይሁንና አደገኛ ጨረር እንዳላገኘንባቸው ሲያረጋግጡ እፎይታ ሳይሰማቸው አልቀረም።»

በፉኩሺማ ያሠጋውን የመርዘኛ ጨረር አደጋ ለመግታት ከቶኪዮና ኦሳካ የዘመቱ ወታደሮችና የእሳት አደጋ መከላከያ ሠራተኞች፤ እጅግ አስከፊውን አደጋ በመከላከል ረገድ የጀግንነት ሙያ እንደፈጸሙ እየተነገረላቸው ነው። ይህን ተጋድሎ ሲፈጽሙ፣ የራሳቸውን ህይወት አደጋ ላይ በመጣል ነው። የአውታሩ ባለቤት TEPCO የተሰኘው ኩባንያ፣ የችግሩን መጠን አቃሎ ለመመልከት ሲጥር ከመሰንበቱም ሌላ ፣ ከውቅያኖስ ወሃ እየጨለፉ የአቶም ኃይል ማመንጫውን ጋን ለማቀዝቀዝ እንኳ በሓሳብ እንዳልተስማማ ነበረ የተገለጠው።

በጃፓን ጠረፍ ፤ በውቅያኖሱ ውሃ፣ የመርዘኛው ጨረር መጠን ከፍ እያለ ነው። TEPCO ከፉኩሺማ በስተደቡብ 100 ኪሎሜትር ረቀት ላይ ውሃ እንዲመረመር ያደረገ ሲሆን፤ በዚያም ከመደበኛው መጠን መርዘኛው ጨረር፤ 25 እጥፍ ከፍ ብሎ መገኘቱ ተደርሶበታል። የጃፓን መንግሥት እስካሁን አደገኛ አካባቢ የሚሰኘው ቀጣና ከፉኩሺማ ማዕከል አንስቶ 25 ኪሎሜትር ዙሪያ እንጂ ከዚያ እንዲሰፋ የሚፈልግ አይመስልም።

በጃፓን መጋቢት 2,2003 ዓ ም፤ በደረሰው የምድር ነውጥና በተከተለው እጅግ ኃይለኛ የውቅያኖስ ማዕበል የሞቱት ቁጥር በዛሬው ዕለት 9,000 መድረሱ ተገልጧል። ከ 12,000 በላይ ደብዛቸው እንደጠፋ ነው። ናቶሪ የተባለችው ከተማ ከንቲባ እንዳሉት የሞቱባቸውን ወገኖቻቸውን አስከሬን ያገኙ ዕድለኞች ናቸው። ከ 7 ዓመት ገደማ በፊት በአንዶኔሺያ በደረሰው ብርቱ የምድር ነውጥና በተከተለው ሱናሚ፤ 37,000 ያህል ሰዎች ደብዛቸው እንደጠፋ የቀረ ሲሆን፤ የወቅያኖሱ ማዕበል አስከሬናቸውን አርቆ እንደወሰደው ነው የሚታሰበው። ይህ በአንዲህ እንዳለ የጀርመን ካቶሊካውያን ጳጳሳት ጉባዔ የፊታችን ዓርብ ፣ ኮሎኝ በሚገኘው ታዋቂ ካቴድራል ማምሻውን በጃፓን በተፈጥሮ አደጋ ህይወታቸውን ላጡት ሁሉ የጸሎት መርኀ ግብር አዘጋጅቷል። በዚያ ሥነ ሥርዓትም ፤ በጀርመን ሀገር የሚኖሩ ጃፓናውያን ማኅበረሰብ እንዲገኝ ተጋብዟል።

በሰሜን ምሥራቅ ጃፓን ፤ በኀያልነቱ ፣ እስካሁን ወደር ያልተገኘለት በሪኽተር መለኪያ 9,0 የደረሰ ብርቱ የምድር ነውጥና እጅግ ኃይለኛ የውቅያኖስ ማዕበል(ሱናሚ)ባለፈው ዓርብ መጋቢት 2, በጃፓን የቀን ስሌት ቅዳሜ፣ መጋቢት 3 ,2003 ከባድ ጥፋት ካደረሰ ወዲህ፣ እስካሁን በይፋው መግለጫ መሠረት ፤ ህይወታቸውን ያጡት 9,000 ሲሆኑ ከ 12,000 በላይ ደግሞ ደብዛቸው እንደጠፋ ነው። በፉኩሺማ የአቶም ኃይል ማመንጫ አውታሮች ለደረሰባቸው ሳንክ መላውን እንዴት ማግኘት አቃተ?እንዴት ብርቱ ጥፋት ሊደርስ ቻለ? የሰሜን ምሥራቅ ጃፓን የወደፊት ዕጣ -ፈንታ ምን ይሆን!?

ተክሌ የኋላ---

በሰሜን ምሥራቅ ጃፓን፣ ፉኩሺማ ላይ ከሚገኙት የአቶም ኃይል ማመንጫ ጋኖች፣ የተደቀነው ሥጋት እስካሁን ሊወገድ አልቻለም። ከአቶም ኃይል ማመንCA አውታሮቹ፤ ጭስ እየወጣና ደመና እየመሰለ ከባቢ አየር ጋር በመቀላቀል ላይ ሲሆን፣ የዓለም አቀፉ የአቶም ኃይል ምንጭ ተቋም ባለሥልጣናት በቦታው በመገኘት፣ አደጋውን ለመግታት የሚደረገውን ጥረት ከመከታተል ባሻገር የአደገኛውን ጨረር መጠን ይለካሉ። ዋና ጽ/ቤቱ በኦስትሩሪያ ፣ ቪየና የሚገኘው የዓለም አቀፉ የአቶም ኃይል ምንጭ ተቋም ባልደረባ ግራሃም አንድርው --

«የመሻሻል ሁኔታ መኖሩን ብናይም፤ በፉኩሺማ ዲቺ ያለው አጠቃላይ ይዞታ አሁንም እጅግ የሚያሳስብ ነው። በአቶም ኃይል ማመንቻዎቹ ጋኖች፣ መጠኑን ያለፈ የመርዘኛ ጨረር ልቀት ማጋጠሙን በመለካት ደርሰንበታል።»

በአቶም ኃይል ማመንጫው ጋን ውስጥ፣ የኑክልየር ማገዶዎቹ ብርቱ ግለት ውሃው እየፈላ እንፋሎት እንዲፈጠር በማድረጉ፤ የአሳት አደጋ ተከላካዮች፤ በሚመጡት ቀናት፣ ውሃ በገፍ እየቀዱ በመቸለስ ለማቀዝቀዝ የሚያደርጉሹትን ጥረት መቀጠል ይኖርባቸዋል። አንድ የጃፓን የአቶም ኃይል አያያዝ ጉዳይ ባለሥልጣን ቃል አቀባይ፤ ተስፋ እንዳደረጉት ከሆነ፣ ለአቶም ኃይል ማመንጫ አውታሮቹ፣ ማቀዝቀዣ አውቶማቲክ መሣሪያ፣ የተቀጠለው ኤልክትሪክ ፣ እስከ ነገ ሊሠራ ይችላል። ማቀዝቀዣው መሣሪያ፣ በኤሌክትሪክ ኃይል እንደገና መሥራት ከጀመረ፣ በአንድ ቀን ውስጥ ተግባሩን በተሣካ ሁኔታ ሊያከናውን ይችላል የሚል እምነት አለ። ኤልክትሪኩ የተቋረጠው፣ በኃይለኛው የምድር ነውጥ እንደነበረ የሚታወስ ነው።

ከፉኩሺማ በስተሰሜን ምሥራቅ 100 ኪሎሜትር ራቅ ብሎ በሚገኘው ቦታ ፤ ዶ/ር ኬይኮ ያማዳ፣ በጭንቀት ላይ የሚገኙ በዛ ያሉ ሰዎችን ፣ የሰውነታቸውን አካላት ምን ያህል አደገኛ ጨረር እንዳገኛቸው በልዩ መሣሪያ ሲመረምሩ ነበረ የሰነበቱት።

«ሰዎቹ ተረብሸዋል። በተቻለ ፍጥነት አካባቢውን ለቀው መጓዝ ነው የሚፈልጉት። ይሁንና አደገኛ ጨረር እንዳላገኘንባቸው ሲያረጋግጡ እፎይታ ሳይሰማቸው አልቀረም።»

በፉኩሺማ ያሠጋውን የመርዘኛ ጨረር አደጋ ለመግታት ከቶኪዮና ኦሳካ የዘመቱ ወታደሮችና የእሳት አደጋ መከላከያ ሠራተኞች፤ እጅግ አስከፊውን አደጋ በመከላከል ረገድ የጀግንነት ሙያ እንደፈጸሙ እየተነገረላቸው ነው። ይህን ተጋድሎ ሲፈጽሙ፣ የራሳቸውን ህይወት አደጋ ላይ በመጣል ነው። የአውታሩ ባለቤት TEPCO የተሰኘው ኩባንያ፣ የችግሩን መጠን አቃሎ ለመመልከት ሲጥር ከመሰንበቱም ሌላ ፣ ከውቅያኖስ ወሃ እየጨለፉ የአቶም ኃይል ማመንጫውን ጋን ለማቀዝቀዝ እንኳ በሓሳብ እንዳልተስማማ ነበረ የተገለጠው።

በጃፓን ጠረፍ ፤ በውቅያኖሱ ውሃ፣ የመርዘኛው ጨረር መጠን ከፍ እያለ ነው። TEPCO ከፉኩሺማ በስተደቡብ 100 ኪሎሜትር ረቀት ላይ ውሃ እንዲመረመር ያደረገ ሲሆን፤ በዚያም ከመደበኛው መጠን መርዘኛው ጨረር፤ 25 እጥፍ ከፍ ብሎ መገኘቱ ተደርሶበታል። የጃፓን መንግሥት እስካሁን አደገኛ አካባቢ የሚሰኘው ቀጣና ከፉኩሺማ ማዕከል አንስቶ 25 ኪሎሜትር ዙሪያ እንጂ ከዚያ እንዲሰፋ የሚፈልግ አይመስልም።

በጃፓን መጋቢት 2,2003 ዓ ም፤ በደረሰው የምድር ነውጥና በተከተለው እጅግ ኃይለኛ የውቅያኖስ ማዕበል የሞቱት ቁጥር በዛሬው ዕለት 9,000 መድረሱ ተገልጧል። ከ 12,000 በላይ ደብዛቸው እንደጠፋ ነው። ናቶሪ የተባለችው ከተማ ከንቲባ እንዳሉት የሞቱባቸውን ወገኖቻቸውን አስከሬን ያገኙ ዕድለኞች ናቸው። ከ 7 ዓመት ገደማ በፊት በአንዶኔሺያ በደረሰው ብርቱ የምድር ነውጥና በተከተለው ሱናሚ፤ 37,000 ያህል ሰዎች ደብዛቸው እንደጠፋ የቀረ ሲሆን፤ የወቅያኖሱ ማዕበል አስከሬናቸውን አርቆ እንደወሰደው ነው የሚታሰበው። ይህ በአንዲህ እንዳለ የጀርመን ካቶሊካውያን ጳጳሳት ጉባዔ የፊታችን ዓርብ ፣ ኮሎኝ በሚገኘው ታዋቂ ካቴድራል ማምሻውን በጃፓን በተፈጥሮ አደጋ ህይወታቸውን ላጡት ሁሉ የጸሎት መርኀ ግብር አዘጋጅቷል። በዚያ ሥነ ሥርዓትም ፤ በጀርመን ሀገር የሚኖሩ ጃፓናውያን ማኅበረሰብ እንዲገኝ ተጋብዟል።

ተክሌ የኋላ

አርያም ተክሌ