ጁልየስ ኔሬሬ የታንዛንያ አባት | ይዘት | DW | 14.08.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ይዘት

ጁልየስ ኔሬሬ የታንዛንያ አባት

በአፍሪቃ የነጻነት ትግል ውስጥ ስማቸው ከሚነሳ ጥቂቶች መካከል ጁልየስ ካምባራጅ ኔሬሬ አንዱ ናቸው፤ በቀድሞ መጠሪያዋ የታንጋኒካ የአሁኗ የታንዛንያ የመጀመሪያው ፕሬዝዳንት። ኔሬሬ በጎርጎሮሳዊው 1961 ዓም ከብሪታንያ ቅኝ አገዛዝ ነጻ የወጣችውን ታንጋኒካን እንዲሁም ከሦስት ዓመት በኋላ ታንጋኒካ እና ዛንዚባር ተዋህደው የመሰረቷትን ታንዛንያን በአጠቃላይ ለ23 ዓመታት መርተዋል። በሥልጣን ዘመናቸው ያራመዱት ሶሻሊስታዊ መርህ ከሀገሪቱ ኤኮኖሚ አመዛኙን ማድቀቁ ቢነገርም አሁንም በታንዛንያ ብሔራዊ ጀግና ተብለው ይወዳሳሉ። ። ጀምስ ማሀንዶ ያዘጋጀውን ኂሩት መለሰ አጠናቅራዋለች።

ቪድዮውን ይመልከቱ። 01:31

በተጨማሪm አንብ