ጀነራል ሰዓረ መኮንንና የብርጋድየር ጀነራል ገዛኢ አበራ ማንነት | ኢትዮጵያ | DW | 24.06.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ጀነራል ሰዓረ መኮንንና የብርጋድየር ጀነራል ገዛኢ አበራ ማንነት

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የፕሬስ ሴክረታርያት የጀነራል ሰዓረ መኮንን የቀብር ስነ ስርዓት አዲስ አበባ እንደሚፈጽም እና የሜጀር ጀነራል ገዛኢ አበራ ስርዓተ ቀብር ደግሞ መቀሌ እንደሚሆን ቢናገሩም የትግራይ ክልል ኮሚኒኬሽን ቢሮ ደግሞ ሁለቱም መቀሌ ይቀበራሉ ሲል አስታውቋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:46

የጀነራሎቹ ስብዕና

ቅዳሜ ምሽት በጠባቂያቸው የተገደሉት የየኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ጠቅላይ ኤታ ማዦር ሹም ጀነራል ሰዓረ መኮንን ከልጅነት እድሜያቸው አንስቶ በሳል እንደነበሩ በቅርብ የሚያውቋቸው ለዶቼቬለ «DW» ተናገሩ። በአጭር ጊዜ ትልቅ ወታደራዊ ልምድ ያካበቱ ጀግና ነበሩ ሲሉም ስለ ጀነራሉ እማኝነታቸውን ሰጥተዋል። በሌላ በኩሉ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የፕሬስ ሴክረታርያት የጀነራል ሰዓረ መኮንን የቀብር ስነ ስርዓት አዲስ አበባ እንደሚፈጽም እና የሜጀር ጀነራል ገዛኢ አበራ ስርዓተ ቀብር ደግሞ መቀሌ እንደሚሆን ቢናገሩም የትግራይ ክልል ኮሚኒኬሽን ቢሮ ደግሞ ሁለቱም መቀሌ ይቀበራሉ ሲል አስታውቋል። የመቀሌው ወኪላችን የጀነራል ሰዓረ እና ከርሳቸው ጋር የተገደሉትን የሜጀር ጀነራል ገዛኢን ማንነት በሚከተለው ዘገባው ያስቃኘናል።

ሚሊዮን ኃይለ ሥላሴ

ኂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ

 

Audios and videos on the topic