ጀርመኖች በእስልምና ላይ ያደረባቸው ስጋት | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 08.01.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አውሮጳ/ጀርመን

ጀርመኖች በእስልምና ላይ ያደረባቸው ስጋት

ከግማሽ በላይ የሚሆኑ ሙስሊም ያልሆኑ ጀርመኖች እስልምና እንደሚያሰጋቸው ይኽው የዳሰሳ ጥናት አሳይቷል ። ይህም ከሶስት ዓመት በፊት ከነበረው ሁኔታ ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ መሆኑ ተዘግቧል ።

ቤርትልስማን የተባለው ተቋም በህዳር ወር ያካሄደው ጥናት እንደሚጠቁመው በጀርመን ከጊዜ ወደ ጊዜ እስልምና ያሰጋናል የሚሉ ጀርመናውያን ቁጥር እያደገ ነው ። ጥናቱ እደጠቆመው እስልምና የሚያስፈራቸው ጀርመናውያን ቁጥር እጎአ በ2012 53 በመቶ ነበር ። አሁን ግን ወደ 57 በመቶ ከፍ ብሏል ።በአሁኑ ጊዜ ከጀርመናውያን 61 በመቶው እስልምና በአውሮፓ ቦታ የለውም የሚል እምነት ነው ያላቸው ይላል የቤርትልስማን የዳሰሳ ጥናት ። ይህን መሰሉ አስተሳሰብ ያላቸው ጀርመናውያን በ 2012 52 በመቶ ያህሉ ብቻ ነበሩ ።ከነዚሁ እስልምና ያሰጋናል ከሚሉት ሰዎች መካከል 40 በመቶ ያህሉ በገዛ ሃገራቸው የውጭ ዜጋ የሆኑ ያህል እንደሚሰማቸው ነው የሚናገሩት ። አንድ አራተኛ የሚሆኑት ማለትም 24 በመቶው ሙስሊሞች ወደ ጀርመን ከመግባት መታገድ አለባቸው የሚል እምነት አላቸው ይላል ጥናት ። 80 ሚሊዮን ህዝብ ያላት ጀርመን አራት ሚሊዮን የሚገመት ሙስሊም የሚኖርባት ሃገር ስትሆን ከመካከላቸው ሶስት አራተኛው ቱርኮች ናቸው ። ጥናቱ እንዳስታወቀው ጀርመን የሙስሊሞችም መኖሪያ ከሆነች በርካታ ዓመታት ቢቆጠሩም በሃገሪቱ ያላቸው ገፅታ አሉታዊ መሆኑን ነው የቤርትልስማን ተቋም ባልደረባ የሚናገሩት ።

በሌላ በኩል ናቱ እንደሚለው ጀርመን ከሚኖሩ ሃይማኖታቸው ከሚያጠብቁ ሙስሊሞች 90 ከመቶው ዲሞክራሲ ጥሩ የአስተዳደር ስርዓት መሆኑን ያምናሉ ። እነዚህ የህብረተሰብ ክፍሎችም በመንግሥትና በህብረተሰቡ ላይ አመኔታቸውን የጣሉ ናቸው ።መጠይቅ ከተደረገላቸው 10 ሙስሊሞች 9 ኙ ሙስሊም ካልሆኑ ጀርመናውያን ጋር በትርፍ ጊዜያቸው እንደሚገናኙ ፤ ከየሁለቱ አንዳቸው ደግሞ ከሙስሊሞች ውጭ ከሆኑ ሰዎች ጋር ቅርበት እንዳላቸው ሃያማኖተኛ ቢሆኑም አቋማቸውም ለዘብተኛ እንደሆነ ነው ጥናቱ የዘረዘረው ። የጥናቱ ውጤት በጀርመን የሙስሊሞች ምክር ቤት ሊቀ መንበር አስፈሪ ብለውታል በርሳቸው አስተያየት ሙስሊሞች ለዴሞክራሲና ለሰብዓዊ መብቶች መከበር እንዲሁም ለነፃነት ያላቸው አድናቆት ዝም ብሎ የሚነገር ብቻ ሳይሆን በህብረተሰቡ ውስጥ ባላቸው ተሳትፎም የሚገለፅ በተግባርም ይታያል ። በውጭ ዜጎች አካባቢ የሚታዩት ወንጀልን የመሳሰሉ ማህበራዊ ችግሮች ህብረተሰቡ እስልምና በተሳሳተ መንገድ እንዲመለከተው ማድረጉንና ይህም መቆም እንደሚገባው ሊቀ መንበሩ አሳስበዋል ።

ኂሩት መለሰ

አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic