ጀርመን፤ የድንበር ቁጥጥር ልትጀምር ነው | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 13.09.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

ጀርመን፤ የድንበር ቁጥጥር ልትጀምር ነው

ጀርመን የስደተኞችን ቀውስ ተከትሎ ጊዜያዊ የድንበር ቁጥጥር ልትጀምር እንደሆነ «ቢልድ» የተሰኘው ጋዜጣ ዘገበ። እንደ ዘገባው ከሆነ ቁጥጥሩ የሚመለከተው የጀርመን እና የኦስትሪያ ድንበርን ይሆናል።

ጀርመን ድንበሯን ለስደተኞች ክፍት ካደረገች አንስቶ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ስደተኞች በኦስትሪያ በኩል አድርገው ጀርመን ገብተዋል። ትናንት ቅዳሜ እስከ እኩለ ሌሊት ብቻ 12,200 ስደተኞች ጀርመን ገብተዋል።በሌላ ዜና በወቅታዊው የስደተኛ ቀውስ ሳቢያ ከኦስትሪያ የሚደረጉ የባቡር ጉዞዎች በሙሉ ወደ ጀርመን መግባት ማቆማቸውን የኦስትሪያ የባቡር ድርጅት ቃል አቀባይ ዛሬ ማምሻውን አስታወቁ።

ልደት አበበ

እሸቴ በቀለ