ጀርመን ወደ ሶርያ የጦር ጄት ለመላክ ማቀድዋ | ዓለም | DW | 26.11.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

ጀርመን ወደ ሶርያ የጦር ጄት ለመላክ ማቀድዋ

እራሱን እስላማዊ መንግሥት እያለ የሚጠራዉን አሸባሪ ቡድን ለመዋጋት በሚደረገዉ የጋራ ጥረት ላይ የጀርመን መንግሥት መረጃ የሚሰበስብ «ቶርናዶ» የተሰኘ ጄትለማሰማራት እንደሚፈልግ ተገለፀ።

ከዚህ ሌላ የጀርመን ባሕር ኃይልም አኤስን ለማጥፋት በሚደረገዉ ጥረት ላይ ለማሰማራት መታቀዱ ነዉ የተገለፀዉ ። ለዚህ ዉሳኔ የጀርመንዋ መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክልና ጉዳዩ የሚመለከታቸዉ ሚኒስትሮች በርሊን ላይ ስብሰባ ተቀምጠዉ እንደነበር የጀርመን የብዙኃን መገናኛ ዘግቦአል። በዉሳኔዉ ስብሰባ ላይ የጀርመንዋ መከላከያ ሚኒስትር ኡርዙላ ፎን ደር ላይን የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፍራንክ ቫልተር ሽታይ ማየር እንዲሁም ምክትል መራሄ መንግስት ዚግማር ገብርኤል እንደተገኙ ተያይዞ ተገልፆአል።

ለዚህ ቅድመ እቅድ የክርስትያን ዲሞክራቲክ ፓርቲና የክርስትያን ሶሻል ፓርቲ እንዲሁም ተጣማሪዉ የሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲ በጋራ መረጃን እንደሚሰጡ ተመልክቶአል። አሸባሪዉን እስላማዊ መንግሥት ለማደን በሚደረገዉ ትግል የጀርመን ተሳትፎ እንደሚጠናከር ባለፉት ጊዚያት የጀርመኗ መራሒተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል መግለፃቸዉና በትግሉም ጀርመን ወታደራዊ ተሳትፎ ልታደርግ እንደምትችልም ሜርክል አመላክተዉ ነበር።

አዜብ ታደሰ

አርያም ተክሌ