ጀርመን በኢትዮጵያዉያን ዓይን | ባህል | DW | 22.11.2012
 1. Inhalt
 2. Navigation
 3. Weitere Inhalte
 4. Metanavigation
 5. Suche
 6. Choose from 30 Languages

ባህል

ጀርመን በኢትዮጵያዉያን ዓይን

ጀርመናዉያን ጠናካራ ሰራተኞች፤ በስነ-ምግባር የታነጹ ፤ትክክለኛ፤ ንጽህናን የሚወዱ፤ በቁጠባ ኑሮአቸዉን የሚመሩ፣ ቀጠሮ አክባሪዎች፤ ረዳቶች መሆናቸዉ በሰፊዉ ይነገርላቸዋል።

በጀርመን ለረጅም ዓመታት የኖሩ እና የጀርመንን ባህል፤ አገረሰባዊ ልማድ፤ እንዲሁም የጀርመናዉያን የኑሮ ዘዴን የተዋወቁ ኢትዮጵያዉያንን፣ «ጀርመናዉያንን እንዴት አገኛችኋቸዉ?» ስንል ዉይይት አድርገን ቅንብር ይዘናል። በጠንካራ ሰራተኝነታቸዉ የሚታወቁት ጀርመናዉያን፤ በሚያመርቱትና ወደ ዉጭ ለገበያ በሚያቀርቡት ቁሳቁሶች እጅግ ተወዳጅ መሆናቸዉ ይታወቃል። ጀርመናዉያን ሁለተኛ ዓለም ጦርነት የወደመዉን ሃገራቸዉን ገንብተዉ፣ የጠፋን ስማቸዉን አድሰዉ፤ ከዓለም መሪ ሀገሮች በቀዳሚነት መሰለፋቸዉ ደግሞ የማይሸሸግ እዉነታ ነዉ። በጀርመን የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ጀርመናዉያንን እንዴት አገኝዋቸዉ፤ በባህሪያቸዉም ሆነ በየዕለት ኑሮአቸዉ? ይህን ጥያቄ ይዤ ብዙም ሳልርቅ የስራ ባልደረባዪ ተክሌ የኋላን ነበር የጠየኩት። ተክሌ የኋላ ጀርመናዉያንን በጀርመን ከሰላሳ አመት በላይ ኖሮ ያዉቃቸዋል። ሰፋ ያለ ማብራርያ ሰጥቶናል። ጀርመናዉያን የከፍተኛ ትምህርታቸዉን በህግ እና በፖለቲካ ሳይንስ እዚሁ ጀርመን ያጠናቀቁት እና ከሃያ አመት በላይ ነዋሪ የሆኑት ዶክተር ለማ ይፍራሸዋ ጀርመናዉያንን ህግን አክባሪዎች፤ ሃገራቸዉን ወዳዶች፣ የሆኑ ጭቅጭቅን የሚሸሹ ፤ ከመናገር ይልቅ መዳመጥን የሚወዱ ናቸዉ ሲሉ ገልጸዉልናል። በቦን ዩንቨርስቲ በእንስሳት ማዳቀል ስራ በረዳት ፕሮፊሰርነት መዕረግ በመምህርነት እና በምርምር ስራ ላይ የሚገኙት ፕሮፊሰር ዳዊት ተስፋዪም ስለ ጀርመናዉያን ያላቸዉን አስተያየት አጫዉተዉናል። እዉነትን መናገር አወንታዊ ተግባር መሆኑን የማንኛዉም ማህበረሰብ ቢገነዘብም ቅሉ ጀርመናዉያን እዉነትን መናገር ግልጽ የመሆን ባህልን ማዳበራቸዉ ይታያል። እንደዉም በአነጋገር ዘይቤያቸዉ «ዉሸት አጭር እግር አለዉ» ሲሉ የዉሸትን አላስፈላጎነት ይገልጻሉ። ማህበረሰቡ የአኗኗር ዘዴን ከጨቅላነቱ እንዲማር በጀርመን የተለያዩ ግዛቶች በሚገኙ የአንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የማህበራዊ አኗኗር ትምህርት እንደሚሰጥ የገለጹት ዶክተር ለማ፤ ህጻናት ስነ-ምግባር እና የአመለካከትን ሁኔታ ይማራሉ።

የጀርመናዉያን ባህል፤ አገረሰባዊ ልማድ፤ ፤እንዲሁም የኗኗር ዘዴ ተሞክሮአቸዉን ካካፈሉን ኢትዮጳያዉያን ጋር ያደረግነዉን ዉይይት የመጀመርያዉን ክፍል ቅንብር ያድምጡ!

አዜብ ታደሰ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic

 • ቀን 22.11.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/16nzc
 • ቀን 22.11.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/16nzc