ጀርመንኛ መማር የሚያስገድደው ህግ 5 ተኛ ዓመት | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 26.06.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

ጀርመንኛ መማር የሚያስገድደው ህግ 5 ተኛ ዓመት

ጀርመን የሚኖርና ለመኖር ያቀደ የውጭ ዜጋ ጀርመንኛ ቋንቋ ማወቅ እንዳለበት እጎአ ከ 2005 ዓም አንስቶ በህግ ተደንግጓል ። በተለይ በትዳር ምክንያት ወደ ጀርመን የሚመጣ የውጭ ዜጋ መሰረታዊ የጀርመንኛ ቋንቋ የመማር ግዴታ ከተጣለበት ደግሞ

Destination Europe – Kapitel-Nr. 8 | Fotograf/Bildagentur: © Simone Perolari/Invision/LAIF | Young African woman | ACHTUNG!! DIE DEUTSCHE WELLE HAT DIE NUTZUNGSRECHTE NUR VOM 15.11.2011 BIS 15.11.2013!! EINSTELLUNGSDATUM: 15.11.2011

ጀርመን የሚኖርና ለመኖር ያቀደ የውጭ ዜጋ ጀርመንኛ ቋንቋ ማወቅ እንዳለበት እጎአ ከ 2005 ዓም አንስቶ በህግ ተደንግጓል ። በተለይ በትዳር ምክንያት ወደ ጀርመን የሚመጣ  የውጭ ዜጋ መሰረታዊ የጀርመንኛ ቋንቋ የመማር ግዴታ ከተጣለበት ደግሞ 5 ዓመታት ተቆጥረዋል ። ይህ በውጭ ዜጎች ላይ የተጫነ ቅድመ ግዴታ አሁንም እያነጋገረ ነው ። የዛሬው አውሮፓና ጀርመን ዝግጅታችን ትኩረት ነው ።

የጀርመን የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት እጎአ ሰኔ 14 2007 ዓም ባሳለፈው ውሳኔ በትዳር ምክንያት ወደ ጀርመን የሚመጣ የውጭ ዜጋ ቢያንስ ለመግባባት የሚያስችለው መሰረታዊ የጀርመንኛ ቋንቋ ማውቅ እንዳለበት ደንግጓል ። ይህ ህግ ሥራ ላይ ከዋለ ወዲህ በጋብቻ ምክንያት ጀርመን ለመምጣት የሚያመልክቱ የውጭ ዜጎች የጀርመን ቪዛ ለማግኘት ባሉበት ሃገር መሰረታዊ የጀርመንኛ ቋንቋ ፈተና ማለፍ ይጠበቅባቸዋል ። ተግባራዊ ከሆነ 5 ዓመታት ያለፈው ይህ ህግ  አሁንም አንዳንድ ጥያቄዎችን ማስነሳቱ አልቀረም  ። ቭላድሚር ክናክ እጎአ በ 1990 ዎቹ አጋማሽ ነበር ከካዛክስታን ወደ ጀርመን ሲመጣ ገና 13 ዓመት ልጅ  ነበር ። ለ 6 ወራት ልዩ የቋንቋ ትምህርት ከተከታተለ በኋላ በቀጥታ ከጀርመን ተማሪዎች ጋር ተቀላቅሎ መደበኛ ትምህርቱን በየደረጃው ቀጥሎ በኢኮኖሚክስ  በዲፕሎም ተመርቋል ። ትምህርቱን ከጨረሰ በኋላ ወደ ሩስያ ለሥራ በሄደበት ወቅት እዚያ ከምትኖረው ጓደኛው ማርያ ጋር ተጋብተው ወደ ጀርመን ለመምጣት ይወስናሉ ።

ማርያ ወደ ጀርመን ከመምጣትዋ በፊት ግን ጀርመንኛ መማርና ፈተናም ማለፍ ነበረባት  ። ትምህርቱን  አጠናቃ ፈተናውንም በቀላሉ አልፋ ወደ ባለቤትዋ አገር ጀርመን መጥታለች ። ይህ ግን ለሁሉም በቀላሉ ላይሳካ ይችላል ። ወይዘሮ ሙሉነሽ ካሴ ጀርመናዊ አግብተው ከነበሩበት ከግሪክ ከባለቤታቸው ጋር ወደ ጀርመን ለመምጣት ሲያመለክቱ  የጀርመንኛ ቋንቋ ትምህርት መከታተልና ፈተናም መውሰድ እንዳለባቸው ተነግሯቸው ተምረው ፈተናም ውስደው ነበር ግን እንዳሰቡት አልሆነላቸውም ።

Eine ehrenamtliche Mitarbeiterin hilft einer Jugendlichen bei der Erstellung einer Bewerbungsmappe, Juli 2011; Copyright: DW/Dennis Stute Für projekt Destination Europe Zuwanderungsgesetz, Bleiberecht, Scheinehe, Integrationskurse, Einbürgerung Der bürokratische Dschungel des Zuwanderungsrechts

ከግሪክ ጀርመን ለመሄድ ተዘጋጅተው ባለመሰካቱ በወቅቱ ያዘኑት ወይዘሮ ሙሉነሽ ግሪክ መቆየት ስላልፈለጉ አዲስ አባባ መጥተው በጎይቴ የባህል ተቋም የጀርመንኛ ትምህርታቸውን ቀጥለዋል

ወይዘሮ ሙሉነሽ ችሎታቸውን መዝነው ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ለመፈተን አስበዋል ።

ወይዘሮ መታሰቢያ አበበ ጀርመን ከሚገኙት ባለቤታቸው ጋራ ትዳር ከመሰረቱ 6 ዓመት ሆኖዋቸዋል ። ርሳቸውም እንዲሁ ባለቤታቸው ወደ ሚገኙበት ጀርመን ለመምጣት በአዲስ አበባው የጎይቴ የባህል ተቋም ጀርመንኛ እየተማሩ ነው ።

ወደ ጀርመን ለመኖር የሚመጡ የውጭ ዜጎች ቋንቋ እንዲማሩ የሚያስገድደው ህግ ሥራ ላይ ከዋለበት ጊዜ አንስቶ በመላው ዓለም የጀርመንኛ ቋንቋ ተማሪ ቁጥር ጨምሯል ። ህጉ እንደወጣ መጀመሪያ ላይ ለፈተና የተመዘገቡት ቁጥር 65 ሺህ ነበር አሁን ደግሞ 40 ሺህ ላይ ረግቷል ከነዚህም ሩብ ያህሉ በቱርኮቹ ከተሞች በኢስታንቡል በአንካራ ና በኢዝሚር ነው ያሉት ።  በአዲስ አበባው የጎቴ የባህል ተቋምም እንዲሁ ከ2007 አንስቶ የተማሪዎች ቁጥር ማደጉን በተቋሙ የቋንቋና የፈተና ክፍል ሃላፊ አቶ ኤርሚያስ ገብረየስ ተናግረዋል ።

በአሁኑ ሰዓት በአዲስ አበባው የጎቴ የባህል ተቋም ወደ 200 የሚሆኑ ተማሪዎች አሉ ። ከነዚህም ጀርመን ለመምጣት የሚፈልጉ A1 የተባለውን በሁለት ኮርስ የሚጠቃለል 14 ሳምንታት የሚፈጅ የቋንቋ ትምህርት መከታተል ና ፈተናም ማለፍ ይጠበቅባቸዋል ። አቶ ኤርሚያስ እንዳሉት በጣም  ለሚቸኩል ደግሞ በ7 ሳምንትም የሚያልቅ ትምህርትም ይሰጣል ። ጀርመን ሃገር ከሚገኝ ቤተሰብ ጋራ ለመቀላቀል የተደነገገው መሰረታዊ የጀርመንኛ ቋንቋን የማወቅ ግዴታ አንዳንዴ በተማሪዎች ላይ ተፅእኖ ማሳደሩ አልቀረም ። ወይዘሮ መታሰቢያ ቋንቋ መማራቸውን አልጠሉትም ። በቋንቋ ምክንያት ተለያይተው መኖሩ ግን ጥሩ አይደለም ባይ ናቸው ። 

NO FLASH NICHT IN FLASH-GALERIEN VERWENDEN!!! ARCHIV - Eine Frau mit Kopftuch schaut sich die Einbürgerungsurkunde der Bundesrepublik Deutschland an, aufgenommen im Rathaus Berlin-Neukölln (Archivfoto vom 12.09.2006). Das neue Zuwanderungsrecht bietet aus Sicht der Frauenrechtsorganisation Terre des Femmes (TdF) keinen ausreichenden Schutz vor Zwangsheiraten. Nach dem am vergangenen Donnerstag (14.06.2007) verabschiedeten Zuwanderungsgesetz müssen Ehepartner aus bestimmten Ländern schon vor der Einreise deutsche Sprachkenntnisse vorweisen. Damit will die Union auch Zwangsheiraten und arrangierten Ehen einen Riegel vorschieben. Die Bundestagsopposition und einige SPD-Abgeordnete sehen in dieser Regelung einen Verstoß gegen den Schutz der Ehe im Grundgesetz. Foto: Peer Grimm dpa/lsw (zu lsw Thema des Tages vom 18.06.2007) +++(c) dpa - Bildfunk+++ dpa nummer 10157974

አንዳንድ ተማሪዎች ቋንቋውን በግዴታ ስለሚማሩና ፈተናውንም እንዲያልፉ ከቤተሰብ በኩል ግፊቱ ስለሚበረታባቸው አንዳንድ ስነ ልቦናዊ ችግሮች እንደሚንፀባረቅባቸው አቶ ኤርሚያስ ገብረየስ ያስረዳሉ ።

ዶክተር ለማ ይፍራሸዋ ግን በዚህ አይስማሙም

ባለፉት 5 ዓመታት ከተገኘው ልምድ በተለያየ የኑሮ ሁኔታ እንዲሁም የትምህርት ደረጃና የመሳሰሉት ልዩነቶች ምክንያት በመደበኛውን የቋንቋ ትምህርት አሰጣጥ ውስጥ የሚያጋጥሙ ችግሮች እንዳሉ እዚህ ጀርመን በፍራንክፈርት ከተማ በመንግሥት በሚደገፍ የውህደት መርሃ ግብር በታቀፈ ትምህርት ቤት ውስጥ የጀርመንኛ ቋንቋ የሚያስተምሩት ዶክተር ለማ ይፍራ ሸዋ ተናገረዋል ።

እነዚህን በመሳሰሉና በሌሎችም ምክንያቶች በተለመደው መርሃ ግብር መሳተፍ ለማይችሉ ተማሪዎች የተለየ መርሃ ግብር ይዘጋጃል ። በአዲስ አበባው የጎቴ ተቋም ይህን መሰሉ አሰራር ተግባራዊ እንደሚሆን ነው አቶ ኤርሚያስ ያስረዱት ።

ድምፅ

5 ዓመት የሞላው ጀርመን ለመመምጣት ቋንቋን ግዴታ ያደረገው ህግ ቤተሰብ እንድ ላይ እንዳይሰባሰብ በማከላከል በተለያዩ የመብት ተሟጋቾች እየተተቸ ነው ። ድንጋጌው የአውሮፓን ህግ ሁሉ ይቃረናል የሚሉት ወገኖች ቋንቋን ባለማወቅ ብቻ ቪዛ መከልከልን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሲሉ ይተቹታል ። ከዚህ ሌላ ህጉ በጀርመን የመኖሪያ ፈቃድ ለማግኘት የሚያመለክቱ የአውሮፓ ህብረት አባል ሃገራትን የዩናይትድ ስቴትስ የጃፓን የአውስትሬሊያና የመሳሰሉትን ዜጎች የቋንቋ ሰርተፊኬት አለመጠየቃቸው ህጉን በአድሎአዊነት እያስተቸው ነው  ።

ሂሩት መለሰ

ተክሌ የኋላ