ጀርመንና የውጭ ዜጎች | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 13.07.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

ጀርመንና የውጭ ዜጎች

ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ በተካሄደው በ19 ነኛው የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ አስደሳች ውጤት ያስመዘገበው የጀርመን ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን የውጭ የዘር ሐረግ ባላቸው ተጫዋቾቹ ብዛት ከእስከዛሬዎቹ ቡድኖች ይለያል ።

default

ከዚህ በወጣት ኃይል ከተገነባው ቡድን 23 ተጫዋቾች 11 መሰረታቸው የውጭ ነው ። ይህ ቡድንም በአንዳንድ አስተያየት ሰጭዎች አባባል የውጭ ዜጎች ከህብረተሰቡ ጋር የመዋሀዳቸውና የጀርመንም ገፅታ የመቀየሩ መገለጫ ተደርጎ ቢወሰድም ሀገሪቱ አሁንም ለውጭ ዜጎች እኩል የትምህርት የስልጠናና የስራ ዕድል በመስጠት ረገድ እጅግ ብዙ ስራ እንደሚጠብቃት ባለፈው ሳምንት የወጣ አንድ የመንግስት ዘገባ አስታውቋል ። የዛሬው አውሮፓና ጀርመን ዝግጅታችን ትኩረት ነው አብረን እንቆይ ።

ሂሩት መለሰ

ተክሌ የኋላ