ጀርመንና የተራቀቀችበት ሥነ-ቴክኒክ፣ | ሳይንስ እና ኅብረተሰብ | DW | 29.05.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ሳይንስ እና ኅብረተሰብ

ጀርመንና የተራቀቀችበት ሥነ-ቴክኒክ፣

ከኢንዱስትሪው አብዮት በኋላ በሚያስደንቅ ፍጥነት ፣ በሥነ ቴክኒክ መጥቀው ከተገኙት ጥቂት አገሮች መካከል አንዷ ጀርመን ናት። እስከ 2ኛው የዓለም ጦርነት ፍጻሜ ድረስ ምናልባትም ቀዳሚዊ ጀርመን ነበረች ማለት ይቻላል ። እርግጥ፤ በ 20ኛው

ክፍለ ዘመን  በዛ ላሉ ዐሠርተ-ዓመታት ፤ በተለያዩ የሳይንስ ዘርፎች ይካሄድ በነበረው ምርምር፣  የመሪነቱን እርፍ ጨብጣ የቆየች ጀርመን እንደነበረች አይካድም። ጀርመን  ተዋኽዳ አንድ ጠንካራ  ሀገር ለመሆን የበቃችው፤   እ ጎ አ በ 1871 ዓ ም  ቢሆንም፣ ከዚያ በፊት ለአያሌ ዘመናት በተለያዩ  አውራጃዎቿ ተመሥርተው የነበሩት ዩንቨርስቲዎቿ ፤ ለምርምር መሥፋፋትና ዕድገት ሰፊ አስተዋጽዖ ማድረጋቸው የሚታበል አይደለም። 

ኖቤል የሰላም ሽልማት እ ጎ አ በ 1901 ዓ ም መሰጠት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ፣ በፊዚክስ ፣ ሥነ ቅመማ(ኬሚስትሪ)እና  በሥነ-ልቡናም ሆነ ህክምና  የ ጀርመንን ያክል የኖቤል ሽልማት የሰበሰበ የለም። በሥነ ቅመማ ብቻ  ፣ ከ 1901 አንስቶ 31 ዓመታት ከቀረቡት የኖቤል ሽልማቶች 14 ቱን ጀርመናውያን ነበሩ ለማሸነፍ የበቁት።  በሃገሪቱ የሚገኙት የምርምር ተቋማትና የምርምር ደጋፊ ድርጅቶች፣ ለተሣካ ወጤትም  ሆነ ግኝት ያበረከቱት በቀላሉ የሚገመት አይደለም። የአልበርት አይንሽታይንና የማክስ ፕላንክ ምርምር  ለዘመናዊው ፊዚክስ  ዓምድ ሲሆን በቬርነር ሃይዘንበርግና  Erwin Schrödinger ተጠናክሮ ነበረ የቀጠለው።  ከእነርሱ በፊት ደግሞ  Hermann von Helmholtz ፣  Joseph von Frauenhofer እና  Gabriel Daniel Fahrenheit ያበረከቱት ድርሻ ሰፊ ነው። 

እ ጎ አ በ 1901 ኖቤል ሽልማት ሲጀመር ፣ በፊዚክስ የመጀመሪያው ተሸላሚ ፤ «ራጅ»ን (X-Ray) የሠራው  Wilhelm Conrad Röntgen ፤ እንዲያውም መታወሻ ይሆነው ዘንድ አንድ የተፈጥሮ ንጥረ ነገር Roentgenium ተብሏል።

ኦቶ ሃን፤የአቶም ጨረርና  የአቶም  ሥነ-ቅመማ ጀማሪ ሊቅ ናቸው። የአቶምን ኃይል ለጥቅም ማዋል  የተቻለውም ከእርሳቸው ምርምር በመነሣት ነው ።

በሂሳብም ጀርመን   በዛ ያሉ  ሊቃውንት ማፍራት የቻለች ሀገር ናት። በኢንጂነሪንግ የጀርመን ዓለም አቀፍ ድርሻ እጅግ የጎላ ነው። በአውሮፓ የመጀመሪያውን አታሚ ማሺን፤ ጆሃንስ ጉዑተንበርግ ከሠራ በኋላ  ኢንጂኔሩ Konrad  Zuse  የመጀመሪያውን ኮምፒዩተር ለመፈልሰፍ በቅተዋል። 

ጀርመን ፤ አዳዲስ ግኝቶችን በሚያበረክቱ፤ በኢንጂኔሮችና ባለኢንዱስትሪዎች ፣ ለምሳሌ ያህል፤  Zeppelin,Daimler,Diesel,Otto,Wankel,Wehrner von Braun እነዚህ ሁሉ ፣ ለሀገሪቱ በተለያዩ ሞተሮች ሥራ ፣ በአየር በረራ ሥነ ቴክኒክ፣  በኅዋ ጉዞ ጅምርም  አቅጣጫ በማስያዝ ሰፊ ድርሻ ያበረከቱ ናቸው። የጀርመን የሥነ ቴክኒክ ምጥቀት ለሲቭል አገልግሎት በሚውሉ የኢንዱስትሪ ውጤቶች ብቻ ሳይሆን፤ በዘመናዊ ጦር መሣሪያም ጭምር መሆኑ የታወቀ ነው። ይህም በመጀመሪያ በ 1870-1871  ከፈረንሳይ  ጋር በተካሄደው ጦርነት ተሻሽሎ የተሠራው ያኔ ዘመናዊ የተባለው ማውዘር (መውዜር)ጠብመንጃ  ለድል ካበቁት  አንዱ ምክንያት እንደነበረ ነው የሚነገረው። ጀርመን በ2ኛው የዓለም ጦርነት በ V-2 ሮኬት፣ ከ2ኛው የዓለም ጦርነት በኋላም ቢሆን፣  በታንክ ፤ በባህር ሰርጓጅ መርከብ ፤ በተለያዩ ዒላማ በማይስቱ ሮኬቶች አሠራር ጀርመን ትልቅ ስም ነው ያላት።

በአሁኑ ጊዜ፤ በሀገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች ከሚገኙት ዘመናዊ  ኢንዱስትሪዎች መካከል ፤ ከዳይምለር ቤንዝ ቀጥሎ በዛ ያሉ ሠራተኞች (1,500 ያህል)ያሉት፣ በኅዋ ምርምር ላይ  ያተኮረው፣ ከአውሮፓው  የአየር መከላከያና የኅዋ ምርምር ኩባንያ (European Defence and Space Company (EADS) 4 አካላት ፣ አንዱ የሆነው ፣ ዋና ማዕከሉ በብሬመን ከተማ የሚገኘው ASTRIUM የተሰኘው ነው።

ይህ እጅግ ዘመናዊ በሆነ ሥነ ቴክኒክና የኅዋ ምርምር  ላይ ያተኮረው «አስትሪየም» ለዓለም አቀፊ የኅዋ ምርምር ጣቢያ ስንቅና ለምርምር የሚበጁ የተለያዩ መሣሪያዎችን ፤ በ ATV  በኩል የሚያቀርብ፤ ኮሎምበስ በተባለችው በዚያው የኅዋ ጣቢያ ለምትገኘው ቤተ-ሙከራም (ላቦራተሪ)ከስበት ኃይል ውጭ በሆነ ቦታ ለሚካሄዱ የተለያዩ ምርምሮች አስፈላጊና ጠቃሚ መሣሪያዎችን ያቀርባል። 

ከትናንት በስቲያ ብሬመን ውስጥ  ASTRIUM  ን  ፣ ጥቂት የዶቸ ቨለ ጋዜጠኞች በጎበኘንበት ወቅት፤  ኩባንያው ስለሚያከናውነው   ሮኬት  የማምምጠቅ፣ ተግባርና ATV (Automated Transfer Vehicle በተሰኘው የተለያዩ የምርምር መሣሪያዎችን) ስለማጓጓዝና የስበት ኃይል በሌለበት በኅዋ ስለሚከናወኑ የተለያዩ ምርምሮች ፤ እንዲሁም በጠፈር አሠሳ ረገድ የአውሮፓ ድርሻ ምን ያህል እንደሆነ  ፣ ከኩባንያው ባለሙያዎች መካከል   Andeas Schütte  የተባሉትን  ጠይቀናቸው ነበር።

EU Raumfahrt ESA ATV Space-Traveller Jules Verne

«ATV በአሁኑ ጊዜ በዛ ያሉ መሣሪያዎችን ለዓለም አቀፉ የኅዋ ምርምር ጣቢያ የሚያደርስ መንኮራኩር  ነው፤ ሰፋ ያለ አገልግሎት ከሚሰጠው ከሩሲያው «ሶዩዝ» ሌላ ማለት ነው---። H-2 የተሰኘው የጃፓን ሮኬትም አለ። ለዓለም አቀፉ የኅዋ ምርምር ጣቢያ ተፈላጊ ነገሮችን የሚያደርስ። የኅዋ ምርምሩን ተግባር እንዲቀጥል ለማድረግ የአውሮፓ ድርሻ በአርግጥ ጠቃሚ ነው። ስለዚህ አዎሮፓ ለዓለም አቀፉ የኅው ምርምር (ISS)ጣቢያ በአነስተኛ  ደረጃ የሚተባበር ሳይሆን አውሮፓውያን ፤ ሙሉ በሙሉ አጋዦች ነን»።

አስትሪዮም ፤ አርያነንና የተለያዩ የመገኛኛ አገልግሎት ሳቴላይቶችንም የሚያመጥቅባቸው 2 ሮኬቶች አሉት። «ቴክሰስ» እና «ማክሰስ» የሚባሉ!

ቴክሰስ 13 ሜትር ርዝማኔ ፤ በአጠቃላይ 2,659 ኪሎግራም ክብደት  ያለውና 400 ኪሎ ዕቃ የሚሸከም ነው።

«ማክሰስ» የተባለው ሮኬት ደግሞ  17 ኪሎግራም ርዝመትና 12,300 ኪሎ ግራም  ክብደት  ያለውና 800 ኪሎ ግራም ክብደት ያለው ዕቃ ለዓለም አቀፉ የኅዋ ምርምር ጣቢያ ማድረስ የሚችል ነው።

ሮኬቶቹ ፤ ሌሎቹም የምርምር መሣሪያዎች ሁሉ የሚሠሩት በብሬመን በሚገኘው «አስትሪየም» ነው። ስለሠራተኞቹ ፣ አንድሪያስ ሹዑተ  እንዲህ ይላሉ።

Erste Galileo-Satelliten erfolgreich gestartet‎

«እዚህ  በዛ ያሉ ጠበብት ናቸው ያሉን። ሰዎቹ፣ ሥራቸውን በጣም የሚወዱ ናቸው። ኅዋን የሚያደንቁ ናቸው። እንደ እኔ! ስለዚህ እያንዳንዱ ስኬታማ ውጤት እንዲገኝ  ነው የሚጥረው። በተለይ በኅዋ አካባቢ ! ያ ደግሞ በጥንቃቄ  ካልተያዘ ክሥረት ነው። አንዲት ትንሽ ስህተት ጠጠቅላላውን ተልእኮ ከንቱ አድርጎ ሊያስቀረው ይችላል። እያንዳንዱ ሴትም ወንድም ሠራተኛ ከልብ ነው ተግባራቸውን የሚያከናውኑት። አንድ ጊዜ ብቻ አይደለም። ሁልጊዜ! በእያንዳንዱ ዕለት ነው ይህን ማከናወን የሚጠበቅባቸው።»

ኅዋን ይበልጥ ለማሰስ ፣ ሌሎች ዓለማትን ፣ ከዋክብትን ለመመርመር፤ የሚደረገው ጥረት የተለያዩ ሃገራትን ትኩረት የሳበ እንደመሆኑ መጠን፤ የአፍሪቃው ክፍለ ዓለም እዚህም ላይ የደቡብ አፍሪቃ ዝግጅት በቀላሉ የሚታይ አይደለም። ኅዋን ለማሰስ፤ በግዛቷ SKA በተሰኘው ጣቢያ የሚተከሉት በዛ ያሉ የሩቁን እጅግ አቅርበው የሚያሳዩ M,ሣሪያዎች (ቴሌስኮፖች) ተከላን በተመለከተ በዓለም አቀፍ  የምርምር ድርጅቶችና ኩባንያዎች ዘንድ ከአውስትሬሊያ ላቅ ያለ ድርሻ የተሰጣት ደቡብ አፍሪቃ ናት። የዘመናዊ ሥነ ቴክኒክ ኩባንያ ፣ አስትሪየም፣  ከአፍሪቃ  ጋር ትብብር የሚያደርግ እንደሁ ላቀረብንላቸው ጥያቄም ሲመልሱ--

«አንዳንዴ እንደሚመስለኝ ፤ የግንዛቤ ጉዳይ  ነው። ያለ አልመሰለኝም። ኅዋና የስበት ኃይል አለመኖር ፤ (ይህ እኛ እንደምናስበው የነበረና ያለ የተፈጥሮ ህግ ነው) አዲስ መንገድ ፤ አቅጣጫ ሊያመላክት  ይችላል።

በቅርቡ የተሠነዘረ ሐሳብና  የተካሄደ ውይይት ነበረ፤ ከደቡብ አፍሪቃ ተወካዮች ጋር!በደቡብ አፍሪቃ የሮኬት መርኀ-ግብር ለመወጠን ወይም ለመደገፍ ግንኙነት አለ። ግን ፤ ሐሳቡ፤ እቅዱ መስፋፋት አለበት።

ይህ ጊዜ ሊወስድ ይችላል።  ግን ፤ እርግጠኛ  ነኝ፣ በጥቂት ዓመታት ውስጥ ፣ ስለዚህ ጉዳይ ብዙ ልንሰማ እንችላለን።»

ተክሌ የኋላ

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic