ጀርመንና ቻይና፣ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 15.01.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

ጀርመንና ቻይና፣

የጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ጊዶ ቬስተርቨለ፣ ዛሬ ቤይጂንግ ከገቡ በኋላ፣ ከቻይናው አቻቸው ያንግ ጂየቼ ጋር በተለያዩ አርእስት ላይ ተነጋግረዋል።

default

ቬስተርቨለ፣ ከቻይናው አቻቸው ያንግ ጂየቼ ጋር፣

የጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ጊዶ ቬስተርቨለ፣ ዛሬ ቤይጂንግ ከገቡ በኋላ፣ ከቻይናው አቻቸው ያንግ ጂየቼ ጋር በተለያዩ አርእስት ላይ ተነጋግረዋል።የጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ጊዶ ቬስተርቨለ፣ ዛሬ ቤይጂንግ ከገቡ በኋላ፣ ከቻይናው አቻቸው ያንግ ጂየቼ ጋር በተለያዩ አርእስት ላይ ተነጋግረዋል።የጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ጊዶ ቬስተርቨለ፣ ዛሬ ቤይጂንግ ከገቡ በኋላ፣ ከቻይናው አቻቸው ያንግ ጂየቼ ጋር በተለያዩ አርእስት ላይ ተነጋግረዋል።ቬስተርቨለ ፣ በቻይና ሰብአዊ መብትና የፕረስ ነጻነት ይሻሻሉ ዘንድ፣ ለእነዚህ ዓላማዎች የሚቆሙ መሆናቸውን የገለጡ ሲሆን፣ የቻይናው ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ፣ ከዚህ አንጻር፣ የተለየ አቋም ያላቸው መሆኑን ነው ያስታወቁት። ቻይናውያን ከአዲሱ የጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ምን ይሆን የሚጠብቁት? የዶቸ ቨለ ባልደረባ ፔትራ አልደንራት ከቤይጂንግ የላከችውን ዘገባ፣ ተክሌ የኋላ እንደሚከተለው አጠናቅሮታል።

ቻይናና ጀርመን የሰብአዊ መብትን አያያዝ በተመለከተ አሁንም የተለያየ አቋም ያላቸው መሆኑ የሚያጠራጥር አልሆነም ። ጊዶ ቬስተርቨለ---

«ውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ባልደረባዬ፣ ለሰብአዊ መብት መቆርቆር፣ ለኅዳጣን መብት፣ ለፕረስ፣ ለንግግርና ጽሑፍ ነጻነት እንዲሁም፣ ለሃይማኖት ነጻነት መቆም፣ በአኛ የውጭ አመራር ዘይቤ፣ ከፍተኛ ዋጋ የሚሰጣቸው እሴቶች መሆናቸውን በሚገባ ያውቃሉ። በዚህ ረገድ በወዳጅነት መንፈስ እንነጋገር አንጂ፣ አቋሜን በግልጽ ነው ያሳወቅሁ።»

የቲቤቱን መንፈሳዊ መሪ ዳላይ ላማን በተመለከተ፣ ያንግ፣ እርሳቸው የፖለቲካ ስደተኛ ናቸው፣ ጥረታቸውም፣ ቲቤትን ነጻ ማውጣት ስለሆነ፣ ቻይና ፈጽሞ አትቀበለውም ብለዋል። ቬስተርቨለ፣ በበኩላቸው፣ የጀርመን ፌደራል መንግሥት የቻይናን ሉዓላዊነት የሚደገግፍ መሆኑን በመጥቀስ፣ በመጪው የካቲት በሙዩኒክ በሚካሄደው ዓለም አቀፍ የፀጥታ ጉባዔ ይገኙ ዘንድ ጋብዘዋቸዋል። ያንግም ፤ በተጠቀሰው ጉባዔ ለመሳተፍ፣ የመጀመሪያው ቻይናዊ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር እንደሚሆኑ አረጋግጠዋል።

ጀርመንና ቻይና የዲፕሎማቲክ ግንኙነት የጀመሩት እ ጎ አ በ 1972 ዓ ም ሲሆን ፣ ቻይና በአሁኑ ጊዜ፣ እስያ ውስጥ ዋንኛዋ የጀርመን የንግድ ደንበኛ ናት ። እንዲሁም፣ በአውሮፓ ዋንኛዋ የቻይና የንግድ ደንበኛ ጀርመን መሆንዋ የሚታበል አይደለም። ሁለቱ አገሮች በንግድ ብቻ ሳይሆን በፖለቲካውም መስክ በየጊዜው የሐሳብ ልውውጥ ያደርጋሉ። ቬስተርቨለ፣ ቻይናን አሁን መጎብኘታቸው ፣ በፔኪንግ ከሚገኙት ዩኒቨርስቲዎች መካከል በውጭ ቋንቋ የሚያስተምረው ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ባልደረባና የጀርመን ጉዳዮች ጠቢብ፣ ሊው ሊኩን እንዲህ ብለዋል። --

«ሥልጣን በተረከቡ በ3ኛው ወር ሄር ቬስተርቨለ ቻይናን መጎብኘታቸው አዲሱ የጀርመን አስተዳደር ፣ አገራቸው ከቻይና ጋር ላላት ግንኙነት ትልቅ ትርጉም እንደሰጡት የሚያመላክት ነው። በጀርመን ሀገር ስለአርሳቸው በሰፊው በአሉታዊነት መልኩ ይነገራል። ነገር ግን፣ የቻይና መገናኛ ብዙኀንም ሆኑ የቻይና ህዝብ ስለቬስትርቨለ ብዙ የሚያውቁት ጉዳይ የለም። »

የቬስተርቨለ ጉብኝት በጥርጣሬ ሳይሆን በአንክሮ ነበረ የተጠበቀው። እርግጥ ነው አ ጎ አ መስከረም 23 ቀን 2007 ዓ ም፣ መራኂተ-መንግሥት ወ/ሮ አንጌላ ሜርክል፣ የቲቤቱን መንፈሳዊ መሪ ተቀብለው ማነጋገራቸው ፣ ቻይናውያንን ያበገነ ጉዳይ እንደነበረ ሊው ሊኩን ካስታወሱ በኋላ ቀጠል በማድረግ--

«መራኂተ-መንግሥት ሜርክል ከጊዜ በኋላ፣ ያኔ ያደረጉት ብልህነትን የሚያንጸባርቅ እንዳልነበረ ተገንዝበዋል። ጠቃሚ ባልሆነ ጉዳይ ፣ ዳላይ ላማን በማቅረብ ቻይናን ማናደድ ባልተገባ ነበር። የያኔው የጀርመን እርምጃ የሁለቱን አገሮች ግንኙነት አቀዝቅዞት ነበር። አዲሱ ውጭ ጉዳይ ሚንስትርም ተመሳሳይ ችግር ነው ያለባቸው። ባለፈው ዓመት ከዳላይ ላማ ጋር ተገናኝተው ነበር። ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ቢሆኑም ምንጊዜም መንሳዊውን መሪ አግኝተው ከማነጋገር የሚገታቸው ነገር እንደሌለ ነው የገለጡት።»

ይህ በግልጽ የተነገረ ዛቻ ነው የሚመስለው። ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ቬስተርቨለ፣ የነጻ ዴሞክራቱ ፓርቲ ሰው ስለ Friedrich Naumann ዕጣ -ፈንታ ነው የተነገራቸው። ድርጅቱ ዳላይ ላማን በመደገፉ፣ እ ጎ አ በ 1966 ዓ ም፣ የቤይጂንግ ጽ/ቤቱ መዘጋቱ አይዘነጋም። ቻይና እስከዛሬ ድረስ፣ ድርጅቱን እንድርሷ አባባል «የቲቤትን ተገንጣዮች» ይደግፋል። ግራም ነፈሰ ቀኝ፣ ቬስተርቨለ ፣ ከአቻቸው ያንግና ከጠ/ሚንስትር ዌን ጋር በሚያደርጉት ውይይት፣ የኤኮኖሚ ግንኙነትን ይበልጥ የመገንባቱ ጉዳይና «የዓለም የአየር ንብረት መዛባት» ላቅ ያለ ግምት የሚሰጣቸው አርእስት ሳይሆኑ አይቀሩም።

ተክሌ የኋላ

አርያም ተክሌ

ተዛማጅ ዘገባዎች