ጀርመናውያን ወጣቶች እና የሥራ አጥነቱ ችግር | ኤኮኖሚ | DW | 05.05.2005
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኤኮኖሚ

ጀርመናውያን ወጣቶች እና የሥራ አጥነቱ ችግር

ጀርመን ባለፉት ስድስት ዓመታት ውስጥ በሥራ ገበያውም ሆነ በኤኮኖሚያዊ ዕድገቱ ዘርፍ ጥሩ ውጤት እንዳላስመዘገበች ተገለፀ።

ይህንን መግለጫ ያወጣው ከጥቂት ጊዜ በፊት ሀያ አንድ ኢንዱስትሪ መንግሥታትን በማወዳደር የሕዝብ አስተያየት መመዘኛ መዘርዝር ያካሄደው የጀርመናውያኑ የቤርትልስማን ተቋም ነው። በተቋሙ ዘገባ መሠረት፡ ጀርመን አሁንም የመጨረሻውን ቦታ እንደያዘች ትገኛለች። በስጳኝ እና በግሪክ የሚታየው የሥራ አጦች አሀዝ ብቻ ነው ከጀርመን ከፍ ብሎ የሚገኘው። በተለይ የወጣቱ ሥራ አጥነት ጉዳይ አሳሳቢ እየሆነ መጥቶዋል። በአሁኑ ጊዜ ከአምስት መቶ ሺህ የሚበልጡ ጀርመናውያን ወጣቶች ሥራ የላቸውም።